የወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ጣቢያ የካይዘን ሥርዓትን ተግባራዊ አደረገ

የወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ጣቢያ የካይዘን ሥርዓትን ተግባራዊ አደረገ

የወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ብክነትን በመቀነስ የሥራ ቅልጥፍናን የሚያሳድገውን የካይዘን የአሠራር ሥርዓት በተግባር ማዋል ጀመረ

የጣቢያው ሥራ አስኪያጅ አቶ ሀብታሙ ግርማ እንደገለፁት በጣቢያው የሚገኙ ልዩ ልዩ የመለዋወጫ ዕቃዎች በካይዘን ፍልስፍና መርሆዎች መሠረት በግምጃ ቤት ውስጥ በሥርዓት እንዲቀመጡና እንዲደራጁ ተደርጓል።

ይህም ዕቃዎቹ ለአገልግሎት በሚፈለጉበት ወቅት ያለ ምንም እንግልትና ጊዜ ሳይባክን በቀላሉ ለማግኘት ከፍተኛ እገዛ ያደርጋል ብለዋል።

ስለ አሠራሩ አስፈላጊነት አቶ ሀብታሙ ሲያብራሩ የካይዘን ሥርዓት መተግበሩ በጣቢያው የሚታዩ አላስፈላጊ የሀብትና የጊዜ ብክነቶችን ሙሉ በሙሉ ለማስቀረት ይረዳል።

አሠራሩ ቁሳቁሶች በዓይነትና በደረጃቸው ተለይተው እንዲቀመጡ ስለሚያስችል የዕቃዎች ደህንነት በአስተማማኝ ሁኔታ እንዲጠበቅና ለረጅም ጊዜ እንዲያገለግሉ ለማድረግ ያግዛል።

ከዚህም በላይ ሠራተኞች በተደራጀና ምቹ በሆነ አካባቢ እንዲሰሩ በማድረግ ለሥራ ተነሳሽነታቸውና ለጣቢያው የዕለት ተዕለት የሥራ ጥራት ቀጣይነት ያለው መሻሻል (Continuous Improvement) ትልቅ ድርሻ እንዳለው ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል።

የወላይታ ሶዶ ኮንቨርተር ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ወደ ጎረቤት አገር ኬንያ የሚላከውን የኤሌክትሪክ ኃይል በማስተላለፍ ረገድ ከፍተኛና ስትራቴጂካዊ ሚና እየተጫወተ የሚገኝ ቁልፍ የኃይል መሠረተ-ልማት ነው።

በመሆኑም በጣቢያው እንዲህ ያሉ ዘመናዊ የአሠራር ሥርዓቶችን መተግበሩ የኃይል አቅርቦቱ አስተማማኝና ያልተቋረጠ እንዲሆን ያደርገዋል በማለት አቶ ሀብታሙ ተናግረዋል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top