⚡️ የሀገር ውስጥ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ማዕቀፋችንን ለማዘመን በምንሰራበት ወቅት አካሄዳችን የፋይናንስ ጽኑነትን ከደንበኞች ማኅበራዊ ደህንነት ጋር ለማጣጣም አራት ዋና ዋና የዲዛይን መርሆዎች ታሳቢ ተደርገዋል።
1️⃣ የኦፕሬሽን ወጪንመሸፈን (Cost Reflectivity):
የገቢ ፍላጎት እና የኦፕሬሽን ወጪዎችን መሸፈን እንደ መነሻ ተወስዷል።
2️⃣ ማህበራዊ ጥበቃ (Social Protection):
ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን የታሪፍ ተጠቃሚ ደንበኞች(Lifeline tariffs) ታሳቢ ያደረጉ የሽግግር ድጋፍ ማእቀፎች ግልጽነት ባለው መልኩ ይተገበራሉ።
3️⃣ የፋይናንስ ጤናማነት (Financial Health):
ተራማጅ በሆነ እና ወጪን የሚሸፍን አሰራር በመተግበር የኃይል አቅራቢ ተቋማትን የፋይናንስ ጤናማነት እና የኢንቨስትመንት አቅም ማጠናከር እንደ አንድ መርህ ታሳቢ ተደርጓል።
4️⃣ የግልጽነት ፍተሻ (Transparency Test):
የተጠናው የታሪፍ ማዕቀፍ ለኢትዮጵያ ኢነርጂ ዘርፍ ቀጣይነት ያለው፣ ፍትሃዊ እና ጽኑ የኃይል ዘርፍ መሰረት መሆንን በማረጋገጥ የፖሊሲውን ውጤታማነት መፈተሽ ላይ ትኩረት ያደርጋል። 🌍🔌