የኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ወጪን ታሳቢ ያደረገ አለመሆኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ

የኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ወጪን ታሳቢ ያደረገ አለመሆኑን የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ

የኤሌክትሪክ ኃይል ታሪፍ ለማምረት የሚወጣውን ወጪ ያማከለ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ።

ዋና ሥራ አስፈፃሚው ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የእንግሊዝ ኤምባሲ ባዘጋጀው የዩኬ-ኢትዮጵያ አረንጓዴ ቴክኖሎጂ ፎረም ላይ እንደተናገሩት በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የሚሸጥበት ታሪፍ ወጪን ያላማከለ ነው።

ከዚህም ባለፈ በኢነርጂ ዘርፉ መዋዕለ ንዋያቸውን ለማፍሰስ የሚፈልጉ ባለሃብቶችን የማያበረታታና በቂ ክፍያ የማያስገኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

በኢነርጂ ዘርፉ ላይ ለተቋሙ አስቸጋሪው ጉዳይ ታሪፍ መሆኑን ዋና ሥራ አስፈጻሚው  ተናግረዋል፡፡

እንደ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገለፃ በዓለም ባንክ አጋዥነት የውጭ አማካሪ በመቅጠር የታሪፍ፣ የማምረቻ ዋጋ እና የኦፕሬሽን ወጪ  ልዩነት ችግሮችን የተመለከተ ጥናት ተደርጓል፡፡

በአማካሪ ድርጅቱ የተዘጋጀውን ጥናት ለኢትዮጵያ ነዳጅና ኢነርጂ ባለሥልጣን እና በየደረጃው ለሚገኙ አካላት በማቅረብ እንደሚገመገም ኢንጂነር አሸብር ጠቅሰዋል፡፡

በዩኬ-ኢትዮጵያ የአረንጓዴ ቴክኖሎጂ ፎረም ላይ በኢነርጂ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ በርካታ የእንግሊዝ የግል ድርጅቶች፣ አማካሪዎችና ሌሎች የመንግሥት ተወካዮች ተገኝተዋል፡፡

“ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”    

Scroll to Top