የኤሌክትሪክ ኃይል ለክልሉ ዕድገት መነቃቃት መሰረት ጥሏል

የኤሌክትሪክ ኃይል ለክልሉ ዕድገት መነቃቃት መሰረት ጥሏል

ኤሌክትሪክ ለአፋር ክልል ኢኮኖሚዊ ዕድገትና ማህበራዊ መነቃቃት መሰረት መጣሉን የክልሉ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ኃላፊ ተናገሩ፡፡

የቢሮ ኃላፊዋ ወ/ሮ አይሻ መሀመድ እንደተናገሩት የኤሌክትሪክ ኃይል ለሰው ልጅ ከሚያስፈልጉ መሰረታዊ ግብዓቶች ውስጥ ወሳኝ በመሆኑ አፋሮች እንደ ዓይን ብሌናቸው የሚያዩት ነው፡፡  

ባለሀብቶች በክልሉ ኢንቨስት ለማድረግ በቅድሚያ የሚጠይቁት የኃይል አቅርቦትን በመሆኑ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በክልሉ እያከናወነ ያለው የኃይል መሰረተ ልማት ሥራ ለባለሃብቶች መተማመኛቸው መሆኑን አንስተዋል፡፡

በክልሉ ያለው ሰላም የኤሌክትሪክ ኃይል መሰረተ ልማቶችን ደኅንነት ለማስጠበቅ ትልቅ ድርሻ ያለው በመሆኑ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅርበት እንደሚሰሩ የቢሮ ኃላፊዋ አረጋግጠዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት በክልሉ ያለው የኤሌክትሪክ ኃይል ባለሀብቶችን እየሳበ መሆኑን የገለፁት ወ/ሮ አይሻ  በቀጣይ እያደገ የሚሄደውን የኃይል ፍላጎቱ ለማሟላት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ፈጣን ምላሽ እንዲሚሰጥ እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top