የኤሌክትሪክ ታሪፍ ድርድር ማዕቀፍን ለማዘመን የተከናወነው ጥናት እየቀረበ ነው

የኤሌክትሪክ ታሪፍ ድርድር ማዕቀፍን ለማዘመን የተከናወነው ጥናት እየቀረበ ነው

የኤሌክትሪክ ታሪፍ ድርድር ማዕቀፍን ለማዘመን የተከናወነው ጥናት ለሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በዛሬው ዕለት በስካይ ላይት ሆቴል እየቀረበ ነው፡፡

የደቡብ ኮሪያ መንግሥት የባለሙያ ድጋፍ በማድረግ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ድርድር ማዕቀፍን ለማዘመን በሚያስችል እና የዕውቀት ሽግግርን ባረጋገጠ አግባብ የተካሄደ ጥናት ነው፡፡

ጥናቱ የኤሌክትሪክ ታሪፍ ድርድር ማዕቀፍ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በማድረግ የተቋሙን የፋይናንስ ቁመና በማጎልበት፣ የግል ኢንቨስትመንቶችን በማበረታታት እና ስጋትን በመቀነስ በኩል ለተቋሙ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተገልጿል።

በጥናቱ የመክፈቻ መርሀ ግብር ላይ በኮሪያ የንግድና ኢንቨስትመንት ፕሮሞሽን ኤጀንሲ  የኢትዮጵያ ከፍተኛ አማካሪ ጥናቱ ሳይንሳዊ መርሆዎችን ባረጋገጠ መልኩ መከናወኑን ገልፀዋል።

በኢትዮጵያ የደቡብ ኮርያ ቻርጅ ዲ አፌር ሚስ ያንግ ሚ ካንግ ከስድስት አስር ዓመታት በላይ የዘለቀውን የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት አንስተው በኃይል ዘርፍ የተጀመረው ግንኙነት የሀገራቱን የወደፊት ግንኙነት ያሳያል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ተወካይ ኢንጂነር ደስታለም ኃይሉ በበኩላቸው የሀገራቱ ግንኙነት አሁን ለተከናወነው የታሪፍ ድርድር ማዕቀፍ ወሳኝ እንደነበር አንስተዋል።

ማዕቀፉ ሙያዊ በሆነ መንገድ በመዘጋጀቱ በዋና ሥራ አስፈፃሚው ስም አመስግነዋል።

Scroll to Top