ኢነርጂ ዛሬ ከቴክኒክና ከኢኮኖሚ ጉዳይ ባለፈ የሀገራትን የውጭ ግንኙነት እና የጂኦፖለቲካዊ ትስስር የሚወስን ዋነኛ የዲፕሎማሲ መሣሪያ እየሆነ መጥቷል። ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል በተለይም በውሃ ሀብት ያላት የመልማት ራዕይ እና እየገነባቻቸው ያሉ ትልልቅ የኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች የሀገራችንን የኢነርጂ ዲፕሎማሲ ከፍ አድርገውታል።
ዓለም አቀፍ ልምዶችን ስንመለከት የኃይል ዲፕሎማሲ ሀገራትን በጋራ ጥቅም ለማስተሳሰር የላቀ ሚና እየተጫወተ መሆኑን እንረዳለን፡፡
- የኖርዌይእናየአውሮፓየኃይልትስስር (Nordic & European Model)
- ኖርዌይ በውሃ ኃይል (Hydropower) ያላትን አቅም በመጠቀም ለጎረቤት አውሮፓ ሀገራት ኤሌክትሪክ ታስተላልፋለች። ይህ የኃይል ንግድ በሀገራቱ መካከል ያለውን የኢኮኖሚ ትስስር በማጠናከር ሰላማዊና የጠበቀ የሁለትዮሽ ግንኙነት እንዲፈጠር አድርጓል።
- የካናዳእናዩኤስየሃይድሮኤሌክትሪክሽርክና (North American Grid Integration)
- ካናዳ ከኪዩቤክ እና ከብሪቲሽ ኮሎምቢያ ግዛቶች የምታመነጨውን የተትረፈረፈ ኤሌክትሪክ ኃይል በድንበር አቋራጭ ማስተላለፊያዎች ለአሜሪካ ግዛቶች በመሸጥ ጠንካራ የኢኮኖሚና የንግድ አጋርነት መስርታለች።
- የኢትዮጵያእናየምስራቅአፍሪካየኃይልማዕከል (East African Power Pool)
- ልክ እንደ አውሮፓና ሰሜን አሜሪካ ልምዶች ሁሉ ኢትዮጵያ ግዙፍ የኃይል ማመንጫዎቿን (እንደ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ እና ሌሎች የውሃ ኃይል ማመንጫና የንፋስ ፕሮጀክቶችን ወደ ሥራ በማስገባት ከምታመነጨው ኃይል ለጎረቤት ሀገራት ኤሌክትሪክ በመሸጥ የውጭ ማንዛሪ በማግኘት የኢነርጂ ዲፕሎማሲ ላይ ቁልፍ ሚና እየተጫወተች ትገኛለች፡፡
የኢነርጂ ሽያጭና የትስስር ማዕቀፍ የሚኖረው ፋይዳ፡-
- የጋራ ዕድገትን ያረጋግጣል፡፡
- የጎረቤት ሀገራትን የኢኮኖሚና የኢንዱስትሪ እንቅስቃሴ በታዳሽ ኃይል እንዲነቃቃና በሰጥቶ መቀበል መርህ ላይ የተመሰረተ የጋራ ዕድገት እንዲጎለብት ያደርጋል።
- አህጉራዊ ውህደትን ያፋጥናል፡፡
- ድንበር ተሻጋሪ የኃይል ንግድ የአፍሪካን ነጻ የንግድ ቀጣና (AfCFTA) ራዕይ በተግባር እውን ለማድረግ ትልቅ መሰረት ይሆናል።
- የሰላምና የዲፕሎማሲ ድልድይ ይሆናል፡፡
- በጋራ የኃይል መሰረተ ልማት የተሳሰሩ ህዝቦች የረጅም ጊዜ ፖለቲካዊ መረጋጋትና አጋርነት ይገነባሉ።
ኢትዮጵያ በታዳሽ ኃይል ማመንጨት ያላት እምቅ አቅም የአፍሪካ የኃይል ማዕከል (Power Hub) እንድትሆን ያስቻላት ሲሆን የኢነርጂ ዲፕሎማሲያችንም ሀገራችንን በአህጉራዊና ዓለም አቀፍ መድረክ ተደማጭነት ከማሳደግ ባለፈ የጋራ ብልጽግናን እውን እያደረገ ይገኛል! 🔌🇪🇹🤝