የኢነርጂ ዘርፍ ሪፎርም – ከተቋማዊ ዕዳ ወደ ፋይናንስ ጥንካሬ!

የኢነርጂ ዘርፍ ሪፎርም – ከተቋማዊ ዕዳ ወደ ፋይናንስ ጥንካሬ!

የሀገራችን የኢኮኖሚ የጀርባ አጥንት የሆነው የኃይል ዘርፍ፣ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ ታሪካዊ የሚባል የሪፎርም እና የፋይናንስ ማሻሻያ እርምጃዎችን አከናውኗል። ከተከናወኑት የሪፎርም ሥራዎች መካከል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የነበረበትን ከፍተኛ የዕዳ ጫና በመቀነስ ረገድ የተከናወኑ ሥራዎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡

🔍 ከሪፎርሙ በፊት የነበረው ተግዳሮት ምን ነበር?

ከ2010 ዓ.ም በፊት የኃይል ዘርፉ በከፍተኛ የንግድ ብድር ዕዳ የተዘፈቀ ነበር፤  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሂሳብ መዝገብ የዕዳና የካፒታል ጥምርታ (Debt-to-equity ratio) ከፍተኛ ልዩነት እንዳለው የሚያሳይ ነበር። ይህ ዕዳ ተቋሙን ለፋይናንስ ሥጋት ከመዳረግ ባለፈ ብድርም ሆነ የግል የኃይል አምራቾችን (IPPs) ለመሳብ እንቅፋት ሆኖ ቆይቷል።

የተወሰዱ ታሪካዊ የማሻሻያ እርምጃዎች፦

  1. የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ (HGER)
  2. ማክሮ ኢኮኖሚውን ለማረጋጋትና የኢነርጂ ዘርፉን የፋይናንስ ዘላቂነት ለማረጋገጥ የተቀረጸ ስልታዊ አጀንዳ ነው።
  1. የዕዳና ሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን (LAMC)
  2. የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ዕዳ “ለመውሰድ” መንግሥት ባቋቋመው የዕዳና ሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን (LAMC) አማካይነት የተቋሙ የሂሳብ መዝገብ (Balance sheet) መልሶ እንዲስተካከል ተደርጓል።
  1. የዕዳ ስረዛና የካፒታል እድገት
  2. በ2016 ዓ.ም ብቻ ወደ 217 ቢሊዮን ብር የሚጠጋ  የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዕዳ ከተቋሙ የሂሳብ መዝገብ እንዲሰረዝ ተደርጓል። ይህም የተቋሙን የተከፈለ ካፒታል ከ319 ቢሊዮን ወደ 589 ቢሊዮን ብር በማሳደግ በሁለት እጥፍ እንዲጨምር አድርጓል።
  1. አስደናቂ የዕዳ ቅናሽ
  2. በመንግሥት ጣልቃ ገብነት የተቋሙ አጠቃላይ የፋይናንስ ዕዳ በ2015 ዓ.ም መጨረሻ ከነበረበት 355 ቢሊዮን ብር በ2016 ዓ.ም መጨረሻ ወደ 128 ቢሊዮን ብር ዝቅ እንዲል ተደርጓል።

💡 የዚህ ለውጥ ፋይዳ ምንድነው?

የተቋሙ የፋይናንስ ጤንነት መመለስ ተቋሙ የብድር ተዓማኒነቱን መልሶ እንዲያገኝ አድርጎታል። ከኪሳራ ወደ ትርፋማነት እንዲሸጋገርም አድርጓል፡፡ በዚህም እንደ ዓለም ባንክ ካሉ ተቋማት ጋር እንደ “ASCENT” ባሉ ግዙፍና አዳዲስ ንጹሕ የኃይል ተደራሽነት መርሀ ግብሮች ላይ ለመሳተፍ በር ከፍቶለታል።

የኢትዮጵያን የኃይል ተደራሽነት ለማሳድና የሀገራችንን የኢንዱስትሪ ሽግግር ለማፋጠን ጠንካራና በፋይናንስ የዳበረ የኃይል ተቋም መገንባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው!

Scroll to Top