የኢትዮጵያ የኢነርጂ ፖሊሲ ሊከለስ ነው

የኢትዮጵያ የኢነርጂ ፖሊሲ ሊከለስ ነው

ከ1986 ዓ.ም ጀምሮ በሥራ ላይ የቆየውን የኢነርጂ ፖሊሲ የሚከልስ ረቂቅ ፖሊሲ ለውይይት ቀረበ።

በውሃና ኢነርጂ ሚኒስቴር አቅራቢነት
በተዘጋጀው የረቂቅ ፖሊሲ ውይይት ላይ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ተሳትፈዋል።

ኢትዮጵያ ስትጠቀምበት የቆየችው የኢነርጂ ፖሊሲ አሁን ካለው የሀገሪቱና የዓለም ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣም ማድረግ አስፈላጊ በመሆኑ በሥራ ላይ ያለውን  ፖሊሲ መከለስ እንዳስፈለገ ተነስቷል።

በረቂቅ ፓሊሲው ላይ ስድስት ዐበይት ጉዳዮች የተካተቱ ሲሆኑ ሙያዊ ድጋፍ በመስጠትና በማማከር የሀገር ውስጥ እና ከሌሎች ሀገራት የተውጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

በተጨማሪም የሌሎች ሀገራት የኢነርጂ ፍጆታና ገቢ ንጽጽር ፣ የዘርፉ የአተገባበር ስርዓት፣ ከትግበራ ጋር  የተገናኙ ተቃርኖዎች፣ በኢነርጂ አቅራቢዎች በኩል ያሉ ውስንነቶችና የመፍትሔ አቅጣጫዎች በግብዓትነት ተወስደዋል።

በውይይቱ ላይ በበይነ መረብ በቀጥታ የተሳተፉ አፍሪካዊያን የኢነርጂ ዘርፍ ባለሙያዎች እና የማህበራት ተወካዮች ለረቂቅ ፖሊሲው ምሉዕነት ገንቢ አስተያየቶችን ሰጥተዋል።

ፖሊሲው ከሀገሪቱ ህጎች ጋር የተጣጣመ መሆኑን ማረጋገጥ እንደሚገባም ነው በውይይቱ ወቅት የተገለፀው።

በረቂቅ ፖሊሲ የውይይት መድረኩ ላይ የፕላንና ልማት ሚኒስትር ዶክተር ፍፁም አሰፋን ጨምሮ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶ/ር ኢንጂነር ሀብታሙ ኢተፋን ጨምሮ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር፣ ከነዳጅና ኢነርጂ ባለስልጣን፣ ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልና ከኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተጋበዙ ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

መረጃው የውሃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ነው።

Scroll to Top