የኢትዮጵያ የኃይል ዘርፍና የግል ባለሀብቶች ተሳትፎ፦ ከውጥን ወደ ተግባር!

የኢትዮጵያ የኃይል ዘርፍና የግል ባለሀብቶች ተሳትፎ፦ ከውጥን ወደ ተግባር!

ኢትዮጵያ የኃይል ማመንጨት ዘርፉን ለግል ባለሀብቶች (Independent Power Producers – IPPs) ክፍት በማድረግ አዲስ ምዕራፍ ጀምራለች። ይህ ታሪካዊ ውሳኔ የሀገሪቱን ታዳሽ የኃይል ፀጋ በግል ባለሀብቶች የፋይናንስና የቴክኖሎጂ አቅም በማልማት የኢኮኖሚ ዕድገታችንን ለማፋጠን ትልቅ ዕድል ይፈጥራል።

🏗⚡️ በዘርፉ ለመሰማራት ተግዳሮቶች አይኖሩም ወይ?

በእርግጥ እንደማንኛውም ግዙፍ ኢንቨስትመንት፣ በኃይል ግዥ ስምምነት (PPA)፣ በመሬት አቅርቦትና በጸጥታ ሁኔታዎች ዙሪያ ፈታኝ ሁኔታዎች ሊያጋጥሙ ይችላሉ። ሆኖም መንግሥት እነዚህን መሠረታዊ እንቅፋቶች ለመቅረፍ ቁርጠኝነቱን በተግባር እያሳየ ይገኛል፡፡

⚡️🇪🇹 የማክሮ-ኢኮኖሚ ማሻሻያ፡
💡 የምንዛሪ ተመን በገበያ እንዲወሰን መደረጉ ባለሀብቶች ትርፋቸውን በቀላሉ ወደ ውጭ መላክ (Repatriation) እንዲችሉ መንገድ ይከፍታል።

⚡️🇪🇹 የታሪፍ ማሻሻያ፡
💡 የኤሌክትሪክ ሽያጭ ዋጋ ከማምረቻ ወጪው ጋር እንዲመጣጠን መደረጉ ፕሮጀክቶች አትራፊና በራሳቸው የሚቆሙ (Bankable) እንዲሆኑ ያስችላል።

⚡️🇪 የPPP ሕግና መዋቅር፡
💡 በመንግሥትና በግል አጋርነት አዋጅ አማካኝነት የባለሀብቱ መብትና ግዴታ በግልጽ ተቀምጧል።

⚡️🇪🇹 የአንድ ማዕከል አገልግሎት፡
💡 ቢሮክራሲን በማሳጠር ባለሀብቶች ፈቃድና መሬት በቀላሉ እንዲያገኙ እየተደረገ ነው።

🏗⚡️ የግል ዘርፉ ተሳትፎ ሲጎለብት የኃይል አቅርቦታችን አስተማማኝነት ያድጋል፡፡ የኢንዱስትሪ ፓርኮቻችን በሙሉ አቅማቸው የሚያመርቱበት ሁኔታ ይፈጠራል፡፡ ሀገራችን የቀጣናው የኃይል ማዕከል የመሆን ራዕይዋ እውን ይሆናል!

Scroll to Top