ኢትዮጵያ በታዳሽ የኃይል ምንጮች የታደለች ሀገር ብትሆንም፣ እስካሁን ጥቅም ላይ የዋለው እምቅ አቅም ከመቶ ሰባት (7%) እንኳን አይበልጥም። ይህ ክፍተት ዘርፉ ለሀገር ውስጥና ለውጭ ኢንቨስትመንት ምን ያህል ክፍት እንደሆነ ማሳያ ነው።
ዋነኞቹን የኃይል አማራጮች፣ ያላቸውን እምቅ አቅም እና በሀገሪቱ ያላቸውን ስርጭት እንደሚከተለው በዝርዝር ማየት ይቻላል፦
የንፋስ ኃይል (Wind Energy)
ኢትዮጵያ በአፍሪካ ከፍተኛ የንፋስ ኃይል እምቅ አቅም ካላቸው ቀዳሚ ሀገራት አንዷ ናት።
💡 አጠቃላይ እምቅ አቅም፦ 1,350 ጊጋ ዋት (GW) በላይ፤
🌱 ተስማሚ አካባቢዎች፦ የንፋስ ፍጥነታቸው በሰከንድ ከ6.5 ሜትር በላይ የሆኑ አካባቢዎች ለኃይል ማመንጫነት ይመረጣሉ። 💨
⚡️ ክልላዊ ስርጭት፦ 📍
o ትግራይ ክልል፦ መቐለና አካባቢው፤
o ሶማሌ ክልል፦ አይሻ (Aysha) — ይህ አካባቢ በሀገሪቱ ከፍተኛው የንፋስ ፍጥነት ያለበት ነው፤ 🌪
o ኦሮሚያ ክልል፦ አዳማ፣ ኢተያ (Iteya) እና የምሥራቅ ሸዋ አካባቢዎች፤
o አማራ ክልል፦ ደብረ ብርሃንና የሰሜን ወሎ አካባቢዎች።
የፀሐይ ኃይል (Solar Energy) ☀️🔅
ኢትዮጵያ በምድር ወገብ አቅራቢያ የምትገኝ በመሆኗ ዓመቱን ሙሉ ከፍተኛ የፀሐይ ብርሃን ታገኛለች።
💡 አጠቃላይ እምቅ አቅም፦ በዓመት 2.1 ሚሊዮን ቴራዋት ሰዓት (TWh)፤ በአማካይ በቀን በአንድ ካሬ ሜትር ላይ 5.5 ኪሎዋት ሰዓት (kWh) ኃይል ማግኘት ይቻላል።
ክልላዊ ስርጭት፦
ከፍተኛ አቅም ያላቸው፦ አፋር፣ ሶማሌ፣ ትግራይ፣ አማራ እና ምሥራቅ ኢትዮጵያ፤
መካከለኛ አቅም ያላቸው፦ ኦሮሚያ እና ደቡብ ኢትዮጵያ።
☀️ ልዩ ባህሪ፦ የፀሐይ ኃይል በየትኛውም የሀገሪቱ ክፍል ከግሪድ ጋር ላልተገናኙ (Off-grid) የገጠር ማህበረሰቦች ተደራሽ ለማድረግ እጅግ አመቺ ነው።
የጂኦተርማል ኃይል (Geothermal Energy) 🌋♨️
ኢትዮጵያ በምሥራቅ አፍሪካ ስምጥ ሸለቆ (Rift Valley) መካከል ላይ በመገኘቷ ከፍተኛ የከርሰ-ምድር እንፋሎት አቅም አላት።
💡 አጠቃላይ እምቅ አቅም፦ ከ 10,000 ሜጋ ዋት (MW) በላይ።
⚡️ ክልላዊ ስርጭት፦ 📍 በዋነኝነት በስምጥ ሸለቆው መስመር ላይ በሚገኙት አፋርና ኦሮሚያ ክልሎች ውስጥ ይገኛል።
🌱 ተስማሚ አካባቢዎች፦ አሉቶ ላንጋኖ (Aluto Langano)፣ ኮርቤቲ (Corbetti)፣ ቱሉ ሞዬ (Tulu Moye) እና ፈንታሌ፤
ጥቅሙ፦ እንደ ንፋስና ፀሐይ ሳይሆን፣ ጂኦተርማል በቀን 24 ሰዓትና ዓመቱን ሙሉ ያለማቋረጥ ኃይል የመስጠት (Base-load) ብቃት አለው።