የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አገኘ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከ2 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አገኘ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ቀደም ሲል የነበረበትን ከፍተኛ የዕዳ ጫና በመቋቋም እና አሠራሩን በማዘመን ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትርፋማነት መሸጋገሩን የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አስታወቀ።

የኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ ( ዶ/ር) እንደገለፁት ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት የመጀመሪያዎቹ ስድስት ወራት ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ትርፍ አስመዝግቧል፡፡

አሁን ላይ የተመዘገበው ትርፍ ተቋሙ ካለበት የብድር ጫና ወጥቶ ራሱን እንዲችል መንገድ የሚከፍት መሆኑ ጠቁመዋል።

ተቋሙ የነበረበት ከፍተኛ የብድር ጫና ወደ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መተላለፉ፣ በመንግሥት የተተገበረው የኢኮኖሚ ሪፎርም እና የተደረገው የታሪፍ ማሻሻያ ለትርፉ መመዝገብ ድርሻው የጎላ መሆኑን ዶ/ር ብሩክ አብራርተዋል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top