ከደቡብ ኢትዮጵያ፣ ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ፣በአማራና ትግራይ ክልሎች የሚስተዋሉ፤ የኃይል መሰረተ ልማት ስርቆት መከላከል፤ የተለያዩ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችን እና መስመሮችን ደህንነት በመጠበቅ የኃይል አቅርቦቱን ማሻሻል በሚቻልባቸው ሁኔታዎች ላይ ምክክር ተደርጓል ።
በተጨማሪም በኃይል መሰረተ ልማት ላይ የሚደርሱ ጉዳቶችን ለመቅረፍና ጉዳት የደረሰባቸውን የማስተላለፊያ መስመሮችን በመጠገን መልሶ ወደ ሥራ ለማስገባት ከትግራይ ባለአደራ አስተዳደር አመራሮች ጋር በቅርበት እየተሰራ ይገኛል፡፡
በቀጣይ ከሸገር ከተማ አስተዳደር እንዲሁም ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል አካላት ውይይቶች የሚቀጥሉ ይሆናል።









