የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ምክንያት የልማት ተነሽ ለሆኑ አርሶ አደሮች የዓይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ምክንያት የልማት ተነሽ ለሆኑ አርሶ አደሮች የዓይነት ድጋፍ አድርጓል፡፡

ኢንጂነር ኤፍሬም ወ/ኪዳን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጀኔሬሽን ቢዝነስ ዘርፍ ም/ል ዋና ሥራ አስፈጻሚበስፍራው ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡ ሲሆን አርሶ አደሮቹ ካሳ ተከፍሏቸው የእርሻ መሬታቸውን ለማመንጫ ጣቢያው የሰጡ ቢሆንም ተቋሙ አርሶ አደሮችን በዘላቂነት መልሶ ለማቋቋም የተለያዩ ድጋፎችን እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።

ከ50-69 በመቶ የሚሆነውን የእርሻ መሬታቸው ለፕሮጀክቱ ግንባታ ሥራ ለሰጡ 13 አርሶ አደሮች 13 በሬዎች እና 144 ኩንታል የመኖ ድጋፍ ተደርጓል።

በተጨማሪም ለአቅመ ደካማና አካል ጉዳተኛ የልማት ተነሽ 76 አርሶ አደሮች አንድ ሺህ ዶሮዎችን ድጋፍ ተድርጓል። የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለዚህ ድጋፍ 4 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር ወጪ አድርጓል።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዚህ ቀደም ከ70 በመቶ በላይ የሚሆነው የእርሻ መሬታቸው ለኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ ግንባታ ለሰጡ አርሶ አደሮች መልሶ ማቆቋሚያ 5 ነጥብ 18 ሚሊዮን ብር ወጭ በማድረግ የወተት ላሞችና የመኖ ድጋፍ ማድረጉ ይታወሳል።

#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል

Scroll to Top