የሽግዳን ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት ይጠናቀቃል።

የሽግዳን ባለ 230 ኪሎ ቮልት የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት ይጠናቀቃል።

ጣቢያው ከኦሞ ኩራዝ የስኳር ፋብሪካ የሚገኘውን ኃይል ወደ ብሔራዊ ቋት ማስገባት የሚያስችል ነው ።

ለአካባቢው ነዋሪዎች ብሎም በመስኖና ሌሎች የልማት ስራዎች ለሚሰማሩ ባለሃብቶች አስተማማኝ ኤሌክትሪክ ኃይል ማቅረብ ያስችላል።

በጣቢያው የትራንስፎርመር ተከላ ሥራ በሙሉ የተጠናቀቀ ሲሆን በመቆጣጠሪያ ክፍሉ የተለያዩ ፓናሎችን የማስቀመጥና ሌሎች መሰረታዊ የሆኑ ተያያዥ ሥራዎች እየተፋጠኑ ነው ።

የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው 400 ሜጋ ቮልት አምፒር ኃይል የመጫን አቅም ያላቸው አምስት ትራንስፎርመሮች እና ሁለት ሻንት ሪአክተሮች እንዲሁም አንድ ባለ 132 እና አስራ አምስት ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች አሉት፡፡

#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል

Scroll to Top