📌 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ሲጠናቀቅ ከ130 ኪሎ ሜትር በላይ በሚረዝሙ የኃይል ማሰራጫ መስመሮች ኤሌክትሪክ እያገኙ ለሚገኙት እንደ ካንጋቴ፣ ቱርሚ እና ኪብሽ ላሉ አካባቢዎች አስተማማኝና ያልተቆራረጠ ኃይል እንዲደርስ ከማድረጉም በላይ የአካባቢውን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴና የቱሪዝም መነቃቃት ለማፋጠን ጉልህ አስተዋጽኦ ያበረክታል።
📌 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያው ከስኳር ፋብሪካው ተረፈ ምርት የሚመነጨውን ኤሌክትሪክ ወደ ብሔራዊ የኃይል ቋት በማስገባት የሀገሪቱን የኃይል አቅም ያሳድጋል።
📌 በአሁኑ ወቅት የመቆጣጠሪያ ሕንፃው፣ የውስጥ ለውስጥ የውሃ ማፋሰሻ መስመሮች እና የሠራተኞች መኖሪያ ቤቶች ግንባታ በመከናወን ላይ ሲሆኑ በቀጣይም ትራንስፎርመሩን ለአገልግሎት ዝግጁ ለማድረግ የዘይት መሙላትና የማጣራት ሥራ ይከናወናል።
📌 ግንባታው ሲጠናቀቅ ጣቢያው አንድ ባለ 132 ኪሎ ቮልት ጥምር ገቢ መስመር፣ አንድ ባለ 50 ሜጋ ቮልት አምፔር ትራንስፎርመር እንዲሁም ኃይልን ወደ ተለያዩ አካባቢዎች የሚያሰራጩ አምስት ባለ 33 ኪሎ ቮልት ወጪ መስመሮች ይኖሩታል።
#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል