የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሁናዊ ገፅታ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አሁናዊ ገፅታ

📌 ከአፍሪካ ሙሉ በሙሉ ታዳሽ ኃይል በመጠቀም 3ኛ የግሪድ አስተዳዳሪ ተቋም ነው።

📌 ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴን እና አሰላ የንፋስ ኃይል ፣ማመንጫን ጨምሮ 20 የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎችን ያስተዳድራል።

📌 ከ20 ሺህ 700 ሰርኪዩት ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው 308 የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን አሉት።

📌 ከ132 ኪሎ ቮልት እስከ 500 ኪሎ ቮልት የቮልቴጅ መጠን ያላቸው 145 የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በኦፕሬሽን ላይ ይገኛሉ። 

📌 በመላው ሀገሪቱ በሚገኙ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ ከ31 ሺህ 400 በላይ ሜጋ ቮልት አምፒር አቅም ያላቸው 361 ትራንፎርመሮች አሉት።

📌 ከ40 ሺህ በላይ የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ተሸካሚ የብረት ምሰሶዎች አሉት።

📌 በአሁኑ ወቅት ካፒታሉ 586 ቢሊየን ብር እንዲሁም አጠቃላይ ሀብቱ ደግሞ 709 ቢሊዮን ብር ደርሷል።

📌 ከአፍሪካ ከውኃ ኤሌክትሪክ ኃይልን በማመንጨት አቅም አንደኛ ነው።

📌 በ2017 በጀት ዓመት 7 ሺህ 910 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም የነበረው ሲሆን በ2018 በጀት ዓመት 9 ሺህ 730 ሜጋ ዋት ኃይል የማመንጨት አቅም ላይ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

Scroll to Top