
ለወራት ከአገልግሎት ውጪ ሆኖ የቆየው የለገጣፎ ማከፋፈያ ጣቢያ ትራንስፎርመር ተጠግኖ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ ሪጅን 1 አስታወቀ፡፡
የሪጅኑ ዳይሬክተር ኢንጂነር ደረጀ ገዛኸኝ እንደተናገሩት በማከፋፈያ ጣቢያው አቅራቢያ በሚጣለው ቆሻሻ ላይ የሚሰባሰቡ አሞራዎች የጣቢያው አንድ ትራንስፎርመር እንዲቃጠል አድርገው ነበር።
በዚህ እና ከስርጭት መስመር ጋር በተያያዙ ቴክኒካል ችግሮች በተደጋጋሚ ኃይል ይቋረጥ እንደነበር ኢንጂነር ደረጀ አንስተዋል።
የኃይል መቋረጡን በዘላቂነት ለመፍታት እና የጣቢያውን አቅም ለማሳደግ አንድ መቶ ሜጋ ዋት የመጫን አቅም ያለው ባለ 125 ሜጋ ቮልት አምፔር ተጨማሪ ትራንስፎርመር ለመትከል የማጓጓዝ ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል።
ትራንስፎርመሩ ተጓጉዞ ማከፋፈያ ጣቢያው እንዲደርስ እገዛ ያደረጉትን የአዲስ አበባ እና የሸገር ከተማ ፖሊስን አመስግነዋል።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

