የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ተቋማዊ አሰራሩን በዘመናዊ ቴክኖሎጂ ሙሉ በሙሉ ለማዘመን የሚያስችለውን «ኢ.ኢ.ፒ ሴንትራል ፖርታል» (EEP Central Portal) በራሱ አቅም አጠናቆ ወደ ትግበራ መሸጋገሩን ይፋ ማድረጉ ይታወሳል።
በተቋሙ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ጽዮን በቀለ በሰጡት ማብራሪያ ይህ አዲስ የዲጂታል ማዕከል ተቋሙን ዘመኑ ከደረሰበት የዲጂታል ቴክኖሎጂ ጋር ለማስተሳሰር ጉልህ አበርክቶ እንዳለው ገልፀዋል።

ወ/ሮ ጽዮን ስለ ኢ.ኢ.ፒ ሴንትራል ፖርታል የሚከተሉትን ሀሳቦች አንስተዋል።
📌 አዲሱ ፖርታል ከተቋሙ ነባር የዲጂታል የአሰራር ሥርዓቶች (እንደ ERP እና የመሳሰሉት) ጋር ሙሉ በሙሉ የመዋሃድ አቅም ያለው ሲሆን መረጃዎችን በቀላሉ ማጋራትና ማስተሳሰር የሚያስችል ነው።
📌 የተቋሙን ሚስጥራዊ ሰነዶች እና መረጃዎች ደህንነት ሙሉ በሙሉ ለመጠበቅ የሚያስችል ጥብቅ የቁጥጥር ሥርዓቶች ተዘርግተውለታል። በዚህም ሰነዶችን ያለፈቃድ ማየት፣ ማተም ወይም ማውረድ (download) እንዳይቻል በደረጃ የተከፋፈሉ ገደቦች ተካትተዋል።
📌 መረጃዎችን ከመጥፋት አደጋ ለመከላከል እና ድንገተኛ ቴክኒካዊ ችግሮችን ለመቋቋም የሚያስችል ሥርዓት አለው።
📌 ማዕከሉ ለተቋሙ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ሽግግር ትልቅ ምዕራፍ የሚከፍት ሲሆን የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂዎችን በሂደት የማካተት ሰፊ ዕቅድም ተይዞለታል።
📌 ሠራተኞች ሥርዓቱን በቀላሉ እንዲጠቀሙበት ለማስቻል ሥልጠናዎች እየተሰጡ ሲሆን የዕለት ተዕለት ሥራዎችን ያለምንም ችግር ለማከናወን ያግዛቸዋልም ተብሏል።
📌ሥርዓቱ በጋራና በትብብር ለመሥራት የሚያስችል አሠራር የተዘረጋለት በመሆኑ ሠራተኞች የውስጥ መረጃዎችን በቀላሉ እንዲለዋወጡ እና የሐሳብ ልውውጥ እንዲያደርጉ የሚያስችል ተቋማዊ ማህበራዊ መድረክ መፍጠሪያ እንዳለው ተናግረዋል፡፡