ከመነጨው ኃይል ውስጥ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ 3 ሺህ 789 ነጥብ 73 ጊጋ ዋት ሰዓት ወይም 50 በመቶ እንዲሁም የጊቤ ሦስት የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ደግሞ 1 ሺህ 21 ጊጋ ዋት ሰዓት ውይም የ13 ነጥብ 5 በመቶ ከፍተኛ ድርሻ ነበራቸው።
በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 7 ሺህ 975 ጊጋ ዋት ሰዓት ለማምረት ታቅዶ 7 ሺህ 567 ነጥብ 66 ጌጋ ዋት ስዓት ኃይል ማምረት ተችሏል። ይህም የዕቅዱን 95 ነጥብ 1 በመቶ መሳካቱን ያሳያል።
በሩብ ዓመቱ ከመነጨው ኃይል 7 ሺህ 388 ነጥብ 17 ጊጋ ዋት ሰዓት ወይም 98 በመቶ ከውሃ እንዲሁም 179 ነጥብ 49 ጊጋ ዋት ሰዓቱ ወይም 2 በመቶ ከንፋስ የተገኘ ነው፡፡
ከተመረተው ኃይል ውስጥ 91 ነጥብ 04 በመቶው ለሀገር ውስጥ ፍጆታ የቀረበ ሲሆን ቀሪው ለጎረቤት ሀገራት ሽያጭ የዋለ ነው።
በሩብ ዓመቱ 17 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያላቸው የአይሻ 2 ንፋስ ኃይል ማመንጫ ሰባት ተርባይኖች ወደ ኦፕሬሽን በመግባታቸው ሀገራዊ የማመንጨት አቅም 9 ሺህ 747 ነጥብ 5 ሜጋ ዋት ደርሷል።

በቀሪ የበጀት ዓመቱ ወራት አማካይ የኃይል ጭነትን በማሻሻል ለበጀት ዓመቱ የታቀደውን የኃይል ምርት ግብ ለማሳካት እንደሚሰራም ተገልጿል::
#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል


