📌 10 ሺህ 314 ኪሎ ሜትር የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮችን ፍተሻ ለማከናወን ታቅዶ 10 ሺህ 247 ኪሎ ሜትር የተከናወነ ሲሆን የ99 ነጥብ 5 በመቶ አፈፃፀም ማስመዝገብ ተችሏል።
📌 የ5 ሺህ 296 ኪሎ ሜትር የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች የጥገና ሥራ በማከናወን የ98 ነጥብ 62 በመቶ አፈፃፀም ማሳካት ተችሏል።
📌 ለ2 ሺህ 586 የማከፋፈያ ጣቢያ ቤዮች ጥገና ለማከናወን ታቅዶ ለ2ሺህ 413 ቤዮች ጥገና በማከናወን የዕቅዱን 93 ነጥብ 33 በመቶ ማሳካት ተችሏል።

📌 ለ4 ሺህ 469 የፕሮቴክሽን ፓነሎች፣ የኮሙኒኬሽን ዕቃዎች እና የስማርት ኢነርጂ ሜትሮች የፍተሻ ስራ በማከናወን የ98 ነጥብ 9 በመቶ አፈፃፀም ተገኝቷል።
📌 ለ2 ሺህ 764 የፕሮቴክሽን ፓነሎች፣የኮሙኒኬሽን ዕቃዎች እና የስማርት ኢነርጂ ሜትሮች የጥገና ሥራዎች በማከናወን የዕቅዱን 99 ነጥብ 5 በመቶ ማሳካት ተችሏል።
📌 በሩብ ዓመቱ ምንም አይነት የሙሉ በሙሉ ኃይል መቋረጥ (Black out) አላጋጠመም።
📌 አጠቃላይ የሩብ ዓመት አፈፃፀም 92 ነጥብ 47 በመቶ ነው።
#የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪክ_ኃይል
