በሩብ ዓመቱ ከኃይል ሽያጭ እና ከፋይበር ኦፕቲክስ ኪራይ 27 ነጥብ 28 ቢሊዮን ብር ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 31 ቢሊዮን ብር ማግኘት የተቻለ ሲሆን ይህም የዕቅዱ 114 በመቶ ነው ።
የተገኘው ገቢ ከአምናው ተመሳሳይ ሩብ ዓመት ጋር ሲነፃፀር የ4 ቢሊዮን ብር ብልጫ አሳይቷል።
በተጨማሪም በሩብ ዓመቱ 60 ነጥብ 9 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ 76 ነጥብ 62 ሚሊዮን ዶላር የተገኘ ሲሆን የ126 በመቶ አፈፃፀም አስመዝግቧል።
ከሀገር ውስጥ ከተገኘው ገቢ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 48 በመቶ፣ የከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች 3 ነጥብ 6 በመቶ፣ የኢትዮ-ጂቡቲ ምድር ባቡር 0 ነጥብ 38 በመቶ እንዲሁም የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች 26 ነጥብ 7 በመቶ ድርሻ አላቸው።
ከጠቅላላ ገቢው የሀገር ውስጥ 78.98 በመቶ ድርሻ ሲኖረው የውጭ ሀገር ደግሞ 21 ነጥብ 02 በመቶ ድርሻ አለው።


