📌 በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ተቋሙ በአይሻ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት በሙሉ አማካሪነት እየሰራ ነው። በተጨማሪም በአሰላ ንፋስ ኃይል ደግሞ በተባባሪ አማካሪነት እየሰራ ይገኛል።
📌 በመጀመሪያው ሩብ ዓመት የ9 የውጪ ኩባንያዎችን ፕሮጀክቶች በአማካሪነት ለመስራት አቅዶ በ5 ፕሮጀክቶች የአማካሪነት ሥራ እያከናወነ ይገኛል።
📌 በሥራ ላይ ከሚገኙ የማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶች መካከል ከ77 በመቶ በላይ የሚሆኑት የአማካሪነት ሥራው በራስ አቅም እየተከናወነ ይገኛል።
📌 19 የማማከር ውል ሥምምነቶችን የማዘጋጀትና ማሻሻል ሥራዎች በተለያዩ የአፈጻጸም ደረጃዎች ላይ ይገኛሉ።
📌 ከግንባታ አስተዳደር እና ከማማከር ሥራዎች በመጀመሪያው ሩብ ዓመት 81 ነጥብ 9 ሚሊዮን ብር ለማግኘት ታቅዶ 71 ነጥብ 5 ሚልዮን ብር ገቢ ማግኘት ተችሏል።
📌 በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በተከናወኑ የማማከር ሥራዎች ተቋሙ ለውጪ አማካሪ ድርጅቶች ያወጣ የነበረውን 198 ነጥብ1 ሚልዮን ብር ድኗል፡፡
📌 በሩብ ዓመቱ ከኢንጅነሪንግ የማማከር ሥራዎች 16 ነጥብ 32 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ/ ገቢ ለማግኘት ታቅዶ 23 ነጥብ 3 ሚልዮን ብር ማግኘት ተችሏል፡፡
📌 በማስተላለፊያ መስመሮችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች ፕሮግራም ውስጥ በግንባታ ላይ ካሉት 37 ፕሮጀክቶች ውስጥ 18 ፕሮጀክቶች ማለትም 50 በመቶ የሚሆኑትን በራስ አቅም እየተገነቡ ነው።