የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የሥራ አመራር አባላት የህዳሴ ግድብን ጎበኙ

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የሥራ አመራር አባላት የህዳሴ ግድብን ጎበኙ

በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የተመራ የሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን ዛሬ ማምሻውን የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጎበኘ፡፡

የሥራ አመራር ቡድኑ በጉብኝቱ 5 ነጥብ 2 ኪሎ ሜትር ዝርመት ያለውን ባለ ኮርቻ ቅርጽ ግድብ እና 1 ነጥብ 8 ኪሎ ሜትር ዝርመት ያለውን ዋናውን ግድብ ጎብኝቷል፡፡

የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሥራ አስኪያጅ ኢንጂነር ክፍሌ ሆሮ እና ሌሎች የፕሮጀክቱና የኦፕሬሽን ኃላፊዎች ስለግድቡ እና ስለ ኃይል ማመንጨት ሥራዎቹ ለጎብኚዎች ገለፃ አድርገዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ የሥራ አመራር አባላት የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በይፋ ተመርቆ ሥራ ከጀመረ በኋላ ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያው ነው፡፡

የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ነገ የካቲት 28 ቀን 2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን የ2018 ግማሽ በጀት ዓመት አፈፃፀም ለመገምገል ዕቅድ ይዟል፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top