
💡ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለዘመናዊነት ቆርጠን መነሳታችን ማሳያ፣ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ምሰሶና የብሔራዊ አንድነት መገለጫ ነው።
💡 ግድቡ ኢትዮጵያውያን ማህበራዊ ስብራቶቻችንን በመጠገን በትናንት ብቻ የምንኮራና በዛሬ የምናፍር እንዳንሆን የሚያደርግ ታሪካዊ ድል ነው።
💡ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የአንድ ወገን የበላይነትን እና ለብቻ ተቆጣጥሮ የመጠቀም ፍላጎት እንዲያከትም በማድረግ በቀጠናው ፍትሐዊ የውሃ አጠቃቀም ሥርዓት እንዲዘረጋ ፈር የቀደደ ነው።
💡ግድቡ ኢንዱስትሪንና እና ዘመናዊ ግብርናን በማስፋፋት የማህበረ ኢኮኖሚ ዕድገት እንዲኖር ወሳኝ ሚና ይጫወታል።
💡ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በሀገራዊ ውክልና/ National symbol/ እንዲሁም በማመንጨት አቅሙ የሀገራዊ ትራንስፎርሜሽን የማዕዘን ድንጋይ ነው።
💡ግድቡ የሚያመነጨውን ያህል ኢነርጂ ለማመንጨት ይወጣ የነበረን ወደ 2 ሚሊዮን ቶን ካርቦንዳይኦክሳይድ በማስቀረት ለዓለም ከባቢ አየር አወንታዊ አስዋጽኦ ያበረክታል።
💡ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ኢትዮጵያውያን በዘመናት መካከል ግጥም እየገጠሙ ዘፈን እየዘፈኑ ቁጭታቸውንና አለመቻላቸውን በሚገልጹበት አባይ ላይ መገንባቱ የተለየ ትርጉም አለው።
💡ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የማንሰራራት ትርክት፣የአንድነት፣የዘመናዊነት እና የኢትዮጵያ ሉዓላዊነት ኩራት መገለጫ ነው። ግድቡ ኢትዮጵያውያን የኢነርጂ ሉዓላዊነታቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኛ መሆናቸውን ማሳያ ጭምር ነው።
💡ኢትዮጵያ አፈሯን እየወሰደ እያየችው ምንም ማድረግ ላልቻለችውና ተቀምጣበት የእሷ መሆን ባልቻለው ሽፍታው አባይ ላይ ግድብ መገንባቷ፤ ኢትዮጵያውያን ተፈጥሮን በተለይም ውሃን መቆጣጠር አይችሉም፣ውሃ እያላቸው ውሃ የሚጠሙና የሚራቡ ህዝቦች ናቸው የሚለውን የጸና ትርክት አሽቀንጥሮ በመጣል የትውልድ የመቻል ማሳያ ነው።
💡ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በላይኛውና በታችኛው ተፋሰስ ጸንቶ የቆየውን ታችኞቹ ይጠቀማሉ ላይኞቹ ውሃውን ይልካሉ የሚለውን ትርክት የበጣጠሰ ነው። በተለይም ውሃ እያላቸው መጠቀም ላልቻሉ የዓለም ህዝቦች የማንቂያ ደወል ነው።
💡የግድቡ መገንባት የናይል ተፋሰስ ሀገራት ጩኸት የቁራ ጩኸት ሆኖ ሰሚ እንዳያገኝ ሲደደረግ የነበረውን የዘመናት ሴራ በአፍ ጢሙ የደፋ ነው።
💡ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የኢትዮጵያ የኢንጂነሪንግ አቅም እንዲሁም የሀገሪቱ የፖሊሲ፣የኮሙዩኒኬሽን እና የዲፕሎማሲ ጥረት ትልቅ ማሳያ ነው።
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”