የዓለም አቀፉ የገንዘብ ድርጅት አይ ኤም ኤፍ ምክትል ዳይሬክተር ኒጌል ክላርክ 1800 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለውን የኮይሻ የውሃ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ጎበኙ፡፡
ምክትል ዳይሬክተሩ ከገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሺዴ እና ከሌሎች የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ፕሮጀክቱን ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
ከጉብኝቱ በኋላ ምክትል ዳይሬክተሩ ኒጌል ክላርክ እንደገለፁት የግድቡ ግንባታ ኢትዮጵያ የጀመረችው ንፁህ፣ ታዳሽ እና ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ለህዝቦቿ እና ለኢንደስትሪዎች ኃይል ለማዳረስ የጀመረችው ሪፎርም አካል ነው፡፡
ይህም ዘላቂ ልማትን ለማረጋገጥ የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”





