የአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ስምምነት ሊፈረም ነው

የአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ስምምነት ሊፈረም ነው

በኢትዮጵያ ከንፋስ ኃይል በማመንጨት አቅሙ ትልቁ የሆነውን የአይሻ አንድ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክት ግንባታ ለማስጀመር የሚያስችል ሥምምነት ሊፈረም ነው፡፡

ዛሬ እንደሚፈረም የሚጠበቀው የሦስትዮሽ የፊርማ ሥነ-ሥርዓት በገንዘብ ሚኒስቴር እና በአልሚው አሜአ ፓወር እንዲሁም በአልሚው እና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል መካከል የሚካሄድ ነው፡፡

300 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቱ በሶማሌ ክልል አይሻ ወረዳ ላይ ይገኛል።

ፕሮጀክቱ በመንግሥት እና በግል አጋርነት ማዕቀፍ የሚገነባ ትልቁና የመጀመሪያው ኢንቨስትመንት ይሆናል።

“ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top