በመላ ሀገሪቱ የሲስተም ማሻሻያ ሥራ እየተከናወነ ነው

በመላ ሀገሪቱ የሲስተም ማሻሻያ ሥራ እየተከናወነ ነው

በመላው ኢትዮጵያ የሲስተም ማሻሻያ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የብሔራዊ ኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።

ማዕከሉ እንደገለፀው በሚከናወነው የሲስተም ማሻሻያ ሥራ በአንዳንድ የሀገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ የኃይል ጭነት በሚበዛባቸው ሰዓታት ዛሬና ነገ የኃይል መቋረጥ ሊያጋጥም ይችላል።

በመሆኑም የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ደንበኞች በሙሉ ችግሩን ተረድተው በትግዕስት እንዲጠብቁና ሌሎች ጊዜያዊ አማራጮችን እንዲጠቀሙ ማዕከሉ ጥሪ አቅርቧል።

“ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top