
ዛሬ ግንቦት 28 ቀን 2016 ዓ.ም የዓለም አካባቢ ጥበቃ ቀን በአለም አቀፍ ደረጃ ለ50ኛ፣ በሀገራችን ደግሞ ለ31ኛ ጊዜ “የተጎዳ መሬት እንዲያገግም የእንክብካቤ ሥራ እንስራ፤ በረሃማነትና ድርቅን ለመቋቋም የመሬት ማገገምን ማረጋገጥ!” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል፡፡
የበዓሉ መከበር በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት የሚያጋጥሙትን ዘርፈ ብዙ ችግሮች አስቀድሞ ለመከላከል የተሰሩ ስራዎች የሚገመገሙበትና ቀጣይ አቅጣጫዎች የሚቀመጡበት ነው፡፡ ሀገራችን ኢትዮጵያም የአካባቢ ጥበቃን ለማጎልበት ከአረንጓዴ ኢኮኖሚ ስትራቴጂ የሚቀዳ የታዳሽ ኃይል ልማት ላይ ትኩረት ሰጥታ በመስራት ላይ ትገኛለች፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የታዳሽ ኃይል አማራጮችን በመጠቀም ሀገሪቱ ለተለያዩ ዓላማዎች የምታውለውን የኤሌክትሪክ ኃይል በማመንጨት እና በማስተላለፍ አረንጓዴ እና ጽዱ ኢትዮጵያን ለመፍጠር በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል።
የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎች መጎልበት የኃይል ማመንጫ ግድቦችን ከደለል በመከላከል፣ የአየር ንብረት እንዳይዛባ እና ተፈጥሯዊ የዝናብ ፍሰት እንዲኖር በማድረግ በቂ የኤሌክትሪክ ኃይል እንዲያመነጭ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡
ስለሆነም እያንዳንዳችን አካባቢያችንን በመጠበቅ የበኩላችንን ሚና እንወጣ መልዕክታችን ነው!
💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”
“ከካርቦን ልቀት የፀዳ አስተማማኝ የኤሌክትሪክ ኃይል!”