የሳፕ ፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ፤

የሳፕ ፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና መስጠት ተጀመረ፤

በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በሁሉም ሪጅኖች ያሉትን የጥገና ሥራዎች ለማዘመን የሚያስችለውንና በሁለተኛው የሳፕ ምዕራፍ ተግባራዊ የሚደረገውን የፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል የተጠቃሚዎች ስልጠና የመጀመሪያ ዙር መስጠት ተጀመረ፡፡

በኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን የቴክኒክ ድጋፍ ቢሮ ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዱ ይማም እንደገለፁት በሁለተኛው ምዕራፍ የሚተገበረው የፕላንት ሜንቴናንስ ሞጁል በኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች ያለውን የጥገና ሥራ ለማዘመን ያስችላል፡፡

በጥገና አሰራር ሥርዓት፣ በመለዋወጫ ዕቃዎች አቅርቦት፣ አስተዳደር እና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ያደረገው የመጀመሪያው ዙር ስልጠና በተግባርና በንድፈ በመታገዝ ለቀጣዮቹ 15 ቀናት እንደሚሰጥ አቶ አብዱ ተናግረዋል፡፡

በሥልጠናው ላይ ከሰባት የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የተውጣጡ የጥገና ኃላፊዎች እና የኤሌክትሪካልና ሜካኒካል መሀንዲሶች እየተሳተፉ ሲሆን በቀጣይ ለሌሎች የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ሠራተኞች ተመሳሳይ ስልጠና እንደሚሰጥ ጠቁመዋል፡፡

ሥልጠናው የኃይል ማመንጫዎች ኦፕሬሽን የቴክኒክ ድጋፍ ቢሮ ከሰው ኃይል ስልጠናና ልማት ቢሮ ጋር በመተባበር የተዘጋጀ ነው፡፡

Scroll to Top