የኃይል አቅርቦት ያልተዳረሰባቸውን አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ነው

የኃይል አቅርቦት ያልተዳረሰባቸውን አካባቢዎች ተደራሽ ለማድረግ እየሰራ ነው

የኃይል አቅርቦቱ ያልተዳረሰባቸውን አካባቢዎች ተደራሽ የሚያደርጉ የኃይል መሰረተ ልማቶች ግንባታ እያከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አስታወቀ።

በተቋሙ የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን እንደተናገሩት እስከ አሁን ምንም ዓይነት የኤሌክትሪክ ኃይል ማከፋፈያ ጣቢያ ያልተገነባባቸውና የኃይል አቅርቦቱ ያልተዳረሰባቸው አካባቢዎች አሉ።

የተደራሽነት ችግርን ለመቅረፍ የሚገነቡት የማከፋፈያ ጣቢያዎችና የማስተላለፊያ መስመሮች እስከ አሁን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ያልነበሩ አካባቢዎችን ታሳቢ ያደረጉ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

የደብባዊ ግሪድ ማስፋፈያ ፕሮጀክት አካል የሆኑት የሺግዳን እና ቲርጋ የማከፋፈያ ጣቢያ ፕሮጀክቶችን ጨምሮ የተደራሽነት ሽፉኑን የሚያሳድጉ የኃይል መሰረተ ልማት ግንባታዎች በመከናወን ላይ መሆናቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል።

እንደ ሀገር ያለውን 54 በመቶ የኤሌክትሪክ ሽፋን ወደ 78 በመቶ ለማሳደግ ተቋሙ ዕቅድ ነድፎ እየሰራ ስለመሆኑ አብራርተዋል።

ቀሪ አካባቢዎች ከግሪድ ጋር ባልተገናኘ መንገድ ኃይል የሚያገኙበትን አቅጣጫ መቀመጡንም ተናግረዋል።

እንደ አቶ ሞገስ ገለፃ ተቋሙ የኤሌክትሪክ ተደራሽነት ሽፋንን የሚያሰፉ አዳዲስ የማከፋፈያ ጣቢያዎችንና ማስተላለፊያ መስመሮችን ከመገንባት በተጓዳኝ ተጨማሪ የኃይል ፍላጎት ባለባቸው አካባቢዎች የአቅም ማሳደግ እና የማዘመን ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከ20 ሺ 650 ሰርኪዩት ኪሎ ሜትር በላይ ርዝመት ያላቸው 307 የማስተላለፊያ መስመሮችን እንዲሁም 194 ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ያስተዳድራል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top