የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል እያደገ የመጣውን የደንበኞች የኃይል ፍላጎት በዘላቂነት ለማሟላትና አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት እንዲኖር ለማድረግ ስትራቴጂካዊ የአቅም ማሳደግ ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።
የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትና የተገኙ ውጤቶች፦
ባለፉት 5 ዓመታት በ10 ቁልፍ ማከፋፈያ ጣቢያዎች ላይ በተከናወኑ የትራንስፎርመር አቅም ማሳደግ ሥራዎች 439 ሜጋ ዋት (ወይም 487.3 MVA) ተጨማሪ ኃይል ወደ ሲስተሙ ማግኘት ተችሏል።
የአቅም ማሳደግ ሥራው የተከናወነባቸው ጣቢያዎች፦
ለገጣፎ፣ ቦሌ ለሚ 2፣ አዳማ 2፣ ወልቂጤ፣ ሚዛን፣ ባህር ዳር፣ ኮምቦልቻ 2፣ ገፈርሳ፣ ባሌ ሮቤ እና አዲስ ዌስት ናቸው።
የአቅም ማሳደግ ሥራዎቹ የቴክኒክ ብልሽቶችን በከፍተኛ ሁኔታ በመቀነስ የኃይል መቆራረጥን ለማስወገድ ትልቅ ውጤት አስመዝግበዋል።
በራስ አቅም የመስራት ስኬት (Expertise):
ይህ ግዙፍ ተግባር በተቋሙ ባለሙያዎች የተከናወነ መሆኑ ለየት ያደርገዋል። ይህም፦
ተቋሙን ከከፍተኛ የውጭ ምንዛሬ ወጪ አድኗል።
ባለሙያዎቹ መሰል ተግዳሮቶችን በራስ አቅም ለመፍታት የሚያስችላቸውን የላቀ ልምድ እንዲያገኙ ረድቷቸዋል።
በአሁኑ ወቅት በቦሌ ለሚ ማከፋፈያ ጣቢያ ተጨማሪ 56.7 ሜጋ ዋት ለማግኘት የሚያስችል የትራንስፎርመር አቅም ማሳደግ ሥራ በትኩረት እየተከናወነ ይገኛል። 🏗
የአቅም ማሳደግ ሥራ የሚኖረው ፋይዳ
የማከፋፈያ ጣቢያዎችን አቅም ማሳደግ ለኢንዱስትሪዎችና ለንግድ እንቅስቃሴዎች የተረጋጋ የኃይል አቅርቦት በመፍጠር ለሀገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት የጀርባ አጥንት ሆኖ ያገለግላል።