የኃይል አቅርቦቱ ለከተሞች የኢንዱስትሪ  ዕድገት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው

የኃይል አቅርቦቱ ለከተሞች የኢንዱስትሪ  ዕድገት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው

የኃይል አቅርቦት አስተማማኝ መሆንና የተደራሽነቱ መስፋት የከተሞችን ሁለንተናዊ ዕድገት እያፋጠነ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የማዕከላዊ 2 ሪጅን መምሪያ ዳይሬክተር ገለፁ፡፡

ዳይሬክተሩ አቶ አለማየሁ ዘበርጋ እንደገለፁት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የገነባቸውና የሚያስተዳድራቸው የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመሮች  ለኢንዱስትሪዎች መስፋፋት ወሳኝ ሚና እየተጫወተ ነው፡፡

በሪጅኑ ውስጥ በሚገኙት በአዳማ ፣ በቢሾፍቱ፣ በሞጆና በዱከም ከተሞች ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ለሀገር ኢኮኖሚዊ ዕድገት ወሳኝ ሚና የሚጫወቱ ኢንዱስትሪዎች ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት የሆነው የኃይል አቅርቦቱ አስተማማኝነት ማደግ እንደሆነ ጠቅሰዋል፡፡

እንደ አቶ አለማየሁ ገለፃ በሪጅኑ ውስጥ በሚገኙ ከተሞች  አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት መኖር ለበርካታ ዜጎች የሥራ ዕድል እንዲፈጠር እና  የኑሮ ዘይቤ እንዲስተካከል  መነቃቃትን ፈጥሯል፡፡

ለህብረተሰቡና ለኢንዱስትሪዎች አስተማማኝ ኃይል ለማቅረብ የሚያስችሉ ከፍተኛ አቅም ያላቸው ማከፋፈያ ጣቢያዎችና ማስተላለፊያ መስመሮች ከአዲስ አበባ እስከ መተሃራ ድረስ ተገንብተው አስተማማኝ አገልግሎት እየሰጡ ነው ብለዋል፡፡

ዱከም ኢስት ኢንዱስትሪ፣ የሱ ብረታብረት፣ ሲ እና ኢ ብራዘርስ ፣ካኖሪያ ጨርቃ ጨርቅ ፣ ጆርጅ ሹዝ እና ወንጂ ስኳር ፋብሪካ በማዕከላዊ 2 ሪጅን ወስጥ ከሚገኙ ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንደስትሪዎች መካከል እንደሚገኙ ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡

የደንበኞችን እርካታ ከማሳደግ ባለፈ ከባለድርሻ አካላት ጋር ተቀራርቦ መስራት  የሪጅኑ የአሰራር ጥንካሬዎች መሆናቸውንም ገልፀዋል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top