በኃይል መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች ለሕግ ቀርበዋል

በኃይል መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች ለሕግ ቀርበዋል

በኃይል መሰረተ ልማት ላይ ስርቆት የፈፀሙ 27 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ሥር አውሎ ለሕግ ማቅረቡን የቢሾፍቱ የከተማ አስተዳደር ገለፀ።

የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና የኢኮኖሚ ክላስተር አስተባባሪ አቶ ገዛኸኝ ደጀኔ እንደገለፁት ከተማዋ ከፍተኛ የኃይል አቅርቦት የሚፈልጉ በርካታ የብረታ ብረትና ማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪዎች መገኛ ናት፡፡

የኃይል መሰረተ ልማቶች በባህሪያቸው ለጥቃት የተጋለጡ በመሆናቸው እና በሚደርስባቸው ጉዳት አገልግሎቱ ቢቋረጥ በከተማዋ ነዋሪዎችና በፋብሪካዎች ላይ ከፍተኛ ኪሳራ የሚያደርስና የከተማዋን ዕድገት የሚያቀጭጭ ነው ብለዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የቴሌኮሙኒኬሽንና የኤሌክትሪክ አውታሮችን ደህንነት ለመጠበቅ በወጣው አዋጅ መሰረት በአካባቢው የሚገኙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የመጠበቅ ኃላፊነት እንዳለበት ተገንዝቦ በትኩረት እየሰራ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በ2017 በጀት ዓመት አስር ወራት ከሚመለከታቸው የፀጥታ አካላት ጋር በቅንጅት በመስራት በኃይል መሰረተ ልማት ላይ ጉዳት ያደረሱ 27 ተጠርጣሪዎችን ለሕግ መቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት በሠራቸው የግንዛቤ ማስጨበጫ ተግባራትና በአጥፊዎች ላይ በሚወስደው የተጠናከረ እርምጃ አሁን ላይ በአካባቢው የነበሩ ችግሮች ሙሉ በሙሉ በሚባል ደረጃ መቀረፋቸውን ገልጸዋል።

የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማቶችን የመጠበቁ ኃላፊነት ለአንድ ተቋም ወይም ለመንግስት ብቻ የሚተው ባለመሆኑ በቀጣይ ሕዝቡን በማሳተፍ መስራት ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑን አስረድተዋል።

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top