የኃይል ምንጮችን ማሰባጠር -የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር!

የኃይል ምንጮችን ማሰባጠር -የኢትዮጵያ የአረንጓዴ ኢነርጂ ሽግግር!

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በውሃ ኃይል (Hydro) ላይ በአብዛኛው የተመሠረተ የኃይል አቅርቦት ሥርዓት ለአየር ንብረት ለውጥ ተጋላጭ መሆኑን በመገንዘብ ባለፉት ሰባት ዓመታት የኃይል ምንጮቹን በንፋስ እና በጂኦተርማል ዘርፎች ኃይል የማሰባጠር (Energy Mix) ሥራዎችን እያከናወነ ይገኛል።

ዋና ዋና ስኬቶች እና በመተግበር ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች፦

  • የንፋስ ኃይል ማመንጫዎች መነቃቃት (Wind Power)፦
  • የአሰላ ፕሮጀክት፦ 100 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው፤
  • የአይሻ 2 ፕሮጀክት፦ በመጀመሪያው ምዕራፍ 80 ሜጋ ዋት የማመንጨት አቅም ያለው፤
  • ስትራቴጂካዊ ፋይዳው፦ የንፋስ ኃይል አብዛኛውን ጊዜ በበጋው ወራት የውሃ ግድቦች መጠን በሚቀንስበት ወቅት ከፍተኛ የማመንጨት አቅም ይኖረዋል። ይህም በደረቃማው ወቅት የኃይል እጥረትን በመከላከል ዓመቱን ሙሉ ለግሪድ መረጋጋት (Grid stability) የላቀ አስተዋፅኦ ያደርጋል።
  • የከርሰ ምድር እንፋሎት (Geothermal) አዲስ ትኩረት፦
  • በስምጥ ሸለቆ ውስጥ የሚገኘውን 10,000 ሜጋ ዋት የሚደርስ የጂኦተርማል እምቅ አቅም ለመጠቀም የአሉቶ ላንጋኖ እና የቱሉ ሞዬ ፕሮጀክቶች በልዩ ትኩረት እየተገነቡ ይገኛሉ። ከፍተኛ የቅድመ ኢንቨስትመንት ወጪና ረጅም ጊዜ የሚጠይቅ ቢሆንም ለሀገሪቱ አስተማማኝ የኃይል ምንጭ እንደሚሆኑ ይታመናል።

የወደፊት ግብ(Target)

ምንም እንኳን ከውሃ የሚመነጨው ኃይል የዘርፉ ዋነኛ ምሰሶ ሆኖ ቢቀጥልም መንግሥት ከውሃ ውጪ ያሉ የታዳሽ ኃይል ምንጮችን (የንፋስ፣ የጂኦተርማል እና የፀሐይ) ድርሻ አሁን ካለበት 5.6% ቢያንስ ወደ 15% ለማሳደግ አልሞ በቁርጠኝነት እየሠራ ይገኛል።

የኃይል ምንጮችን ማሰባጠር የሚኖረው ፋይዳ፦

የኃይል ምንጮችን ማሰባጠር የተፈጥሮ መዛባትንና ድርቅን ተቋቁሞ ለኢንዱስትሪዎች፣ ለከተሞችና ለገጠር ማህበረሰብ አስተማማኝና ያልተቋረጠ ብርሃን ለመስጠት ዋነኛው መፍትሔ ነው!

Scroll to Top