ታዳሽ ኃይል-የአምራች ኢንዱስትሪው ዕድገት የጀርባ አጥንት!

ታዳሽ ኃይል-የአምራች ኢንዱስትሪው ዕድገት የጀርባ አጥንት!

በኢትዮጵያ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ተከትሎ ግብርና፣ ማዕድን፣ ቱሪዝም እና ኢንዱስትሪ ዘርፎች ላይ ትኩረት ተደርጎ በመሰራቱ ታላላቅ ስኬቶች እየተመዘገቡ ይገኛሉ።

ከእነዚህ መካከል ለአምራች ኢንዱስትሪው ዕድገት ወሳኝ ግብዓት የሆነውን የኤሌክትሪክ ኃይል በአስተማማኝ ሁኔታ በማቅረብ ረገድ የኃይል አቅርቦት ዘርፉ ታሪካዊ ምዕራፍ ላይ ይገኛል።

ሀገራችን አረንጓዴ ኢኮኖሚን የመገንባትና ኢትዮጵያን የአፍሪካ የኃይል ማዕከል የማድረግ ራዕይ በመሰነቅ የውሃ፣ የንፋስ፣ የፀሐይ እና የጂኦተርማል ኃይል ማመንጫ ግዙፍ ፕሮጀክቶችን ለአገልግሎት አብቅታለች፡፡ የኮይሻን ጨምሮ በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶችም በተስፋ ሰጪ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

የተመዘገቡ ታላላቅ ስኬቶች በቁጥር እና በተግባር፦

  • የኃይል አቅም እጥፍ ዕድገት፦
  • የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር ኢ/ር ሀብታሙ ኢተፋ እንደገለጹት ከለውጡ ወዲህ የሀገሪቱ የኃይል አቅርቦት ከእጥፍ በላይ አድጓል። ቀደም ሲል ከ4 ሺህ ሜጋ ዋት ያልበለጠው የኃይል ማመንጨት አቅም አሁን ላይ ወደ 10 ሺህ ሜጋ ዋት እየተጠጋ ይገኛል!
  • የኢንዱስትሪ ፍላጎት ምላሽ፦
  • በአሁኑ ወቅት የሚመረተው ታዳሽ ኃይል በዚህ ዓመት 23 በመቶ ላደገው የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪዎች የኃይል ፍላጎት ሙሉ ምላሽ መስጠት ችሏል።
  • የአመራር ቁርጠኝነት ማሳያ፦
  • ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ የነበሩበትን በርካታ ውስብስብ ችግሮች በመፍታት ለብርሃን እንዲበቃ የተደረገ ሲሆን ይህም ለሀይድሮ ኤሌክትሪክ ዘርፍ ግዙፍ አቅም ፈጥሯል።
  • የኃይል ምንጮች መበራከት፦
  • ከሃይድሮ ኤሌክትሪክ ባሻገር በቅርቡ ተመርቆ ለአገልግሎት የበቃውን የአሰላ የንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን ጨምሮ በርካታ የንፋስና የፀሐይ ኃይል አማራጮች በተግባር እየዋሉ ነው።

የኢኮኖሚ ሽግግር ሞተር፦

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተደጋጋሚ እንደገለፁት ኢትዮጵያ የማኑፋክቸሪንግ ማዕከል እንድትሆን በቂ ንጹህና ታዳሽ ኃይል ማምረት ለኢንዱስትሪው ወሳኝና አንገብጋቢ ጉዳይ ነው።

ይህ በታዳሽ ኃይል ዘርፍ የተመዘገበው ስኬት ምርታማነትን ከመጨመር እና ሰፊ የሥራ ዕድል ከመፍጠር ባለፈ ሀገራዊ ኢኮኖሚያችን ከግብርና ወደ ኢንዱስትሪ ለሚያደርገው መዋቅራዊ ሽግግር የላቀ አስተዋጽኦ እያበረከተ ይገኛል። መንግሥት በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ይህንን ዘርፍ ይበልጥ ለማጠናከር ግልጽ ዕቅዶችን አስቀምጦ ወደ ተግባር ገብቷል።

የጋራ ተጠቃሚነትን የሚያረጋግጠው የ”መደመር” ፍልስፍና ውጤት አንዱ ዘርፍ ለሌላው የህልውና መሰረት የሚሆንበትን ምቹ ሁኔታ ፈጥሯል!

Scroll to Top