የተቋሙ የሥራ አመራር አባላት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሚዲያ ኮምፕሌክስን ጎበኙ

የተቋሙ የሥራ አመራር አባላት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሚዲያ ኮምፕሌክስን ጎበኙ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻና የሥራ አመራር አባላት ትናንት የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የሚዲያ ኮምፕሌክስን ተዟዙረው ጎብኝተዋል።

ጉብኝቱ በተቋማቱ መካከል የተጀመሩ የትብብር ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል ያለመ ነው።

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሥራ አመራር አባላት የኮርፖሬሽኑን የተለያዩ የሬዲዮና የቴሌቪዥን ስቱዲዮች እና መቆጣጠሪያ ክፍሎች እንዲሁም የቤተ-መፅሐፍትና የአውደ- ርዕይ ማሳያ ቦታዎችን ጎብኝተዋል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top