ከፍተኛ ጭነት በሚበዛባቸው ሰዓታት እስከ 10 በመቶ የኃይል መቋረጥ ሊያጋጥም ይችላል

ከፍተኛ ጭነት በሚበዛባቸው ሰዓታት እስከ 10 በመቶ የኃይል መቋረጥ ሊያጋጥም ይችላል

በግሪድ ላይ ባጋጠመ የሲስተም ችግር የተነሳ ከፍተኛ ጭነት በሚበዛበባቸው ሰዓታት እስከ 10 በመቶ የሚደርስ የኃይል መቋረጥ ሊያጋጥም እንደሚችል በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የብሔራዊ ኃይል መቆጣጠሪያ ማዕከል አስታወቀ።

በማዕከሉ የሪል ታይም ኦፕሬሽን ሥራ አስኪያጅ አቶ ጉልላት እንግዳ እንዳስታወቁት ያጋጠመውን የቴክኒክ ችግር በፍጥነት ለመቅረፍ የሚያስችሉ ተግባራት በመከናወን ላይ ናቸው።

በመሆኑም የተጀመረው ሥራ እስኪጠናቀቅ ድረስ ህብረተሰቡና ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ደንበኞች በትዕግስት እንዲጠብቁ ሥራ አስኪያጁ ጠይቀዋል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top