የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ከኃይል ሽያጭና ገቢ ጋር በተያያዘ ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ ለመገናኛ ብዙኃን በሰጡት መግለጫ ከኃይል ሽያጭና ገቢ ጋር በተያያዘ ያነሷቸው ዋና ዋና ጉዳዮች

📌 በ2017 በጀት ዓመት ለሀገር ውስጥና ለውጭ ሀገራት ከቀረበ የኃይል ሽያጭ እንዲሁም ከተለያዩ የገቢ ምንጮች 75 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ ተገኝቷል።

📌 ከዚህ ውስጥ 74 ነጥብ 05 ቢሊየን ብሩ  ከኃይል ሽያጭ 1 ነጥብ 41 ቢሊየን ብሩ ደግሞ ከተጓዳኝ አገልግሎቶች የተገኘ ነው።

📌 ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ ከተገኘው ገቢ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 35 በመቶ፣ የዳታ ማይኒንግ 39 በመቶ እንዲሁም የከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች የ4 በመቶ ድርሻ አላቸው።

📌ለውጭ ሀገራት ከቀረበው የኃይል ሽያጭ የተገኘው ገቢ የኬኒያ የ15 በመቶ እንዲሁም የጅቡቲ  5 በመቶ ድርሻ ያለው ነው ።

📌በበጀት ዓመቱ ለደንበኞች በአጠቃላይ 25 ሺህ 180 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ተሽጧል።

📌ከዚህ ውስጥ 93 በመቶ ለሀገር ውስጥ እንዲሁም 7 በመቶ ለውጭ ሀገራት የቀረበ ነው። ይህም ተቋሙ ለሀገር ውስጥ ፍጆታ ቅድሚያ እየተሰጠ ለመሆኑ ማሳያ ነው።

📌ከሽያጭ ከቀረበው ኃይል ውስጥ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት 60 በመቶ፣ የዳታ ማይኒንግ 27 በመቶ፣  ከፍተኛ ኃይል ተጠቃሚ ኢንዱስትሪዎች 6 በመቶ ፣ ለኬኒያ የ5 በመቶ እንዲሁም ለጅቡቲ  2 በመቶ የቀረበ ነው።

📌የተቋሙ ገቢ ከጊዜ ወደ ጊዜ ዕድገት እያሳየ ነው።  ለአብነትም በ2015 በጀት ዓመት ከነበረበት 22 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር በ2017 በጀት ዓመት 75 ነጥብ 4 ቢሊዮን ደርሷል።

📌የተቋሙ ገቢ እያደገ በመሄዱ ለፕሮጀክቶች የሚያስፈልጉ ወጭወችን በራስ አቅም መሸፈን ተጀምሯል። በዚህም በበጀት ዓመቱ 261 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር በራስ አቅም ለፕሮጀክቶች ውሏል።

📌 በበጀት ዓመቱ ከኤሌክትሪክ የኃይል ሽያጭ 338 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሪ ተገኝቷል። ይህም በ2016 በጀት ዓመት ከተገኘው የ140 ሚሊዮን ዶላር ጋር ሲነፃፀር 135 በመቶ ብልጫ ያለው ነው።

📌በበጀት ዓመቱ ለተገኘው ገቢ እና የውጭ ምንዛሪ አፈፃፀም ዕድገት ምክንያቶች:-

📌 የታሪፍ ማሻሻያ መደረጉ፣

📌የዳታ ማይኒንግና የውጭ የኃይል ሽያጭ ገቢ ማደጉ

📌 በሀገር ውስጥ ለዳታ ማይኒንግ ኃይል በዶላር መሸጡ

የ2018 በጀት ዓመት ገቢ ዕቅድ በተመለከተ

📌ተቋሙ በ2018 በጀት ዓመት  ከ109 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ለማግኘት አቅዷል

📌በተያዘው የበጀት ዓመት ከውጭ ምንዛሪ 420 ሚሊዮን ዶላር  ለማግኘት ዕቅድ ይዟል ፡፡

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top