የተቋሙ ካፒታል 709 ቢሊዮን ብር ደረሰ

የተቋሙ ካፒታል 709 ቢሊዮን ብር ደረሰ

………///……..
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አጠቃላይ ሀብት 709 ቢሊዮን ብር መድረሱን በተቋሙ የፋይናንስ ዘርፍ ሥራ አስፈፃሚ አስታወቁ፡፡

ሥራ አስፈፃሚው አቶ ደመረ አሰፋ እንደተናገሩት ተቋሙ ካለው ከ709 ቢሊዮን አጠቃላይ ሀብት መካከል 586 ቢሊዮን ብሩ የተከፈለ ካፒታል ነው፡፡

ተቋሙ በመንግስት እና በራሱ ባከናወናቸው የኢኮኖሚ ሪፎርም ትግበራ የተቋሙን ዕዳ ከ55 በመቶ ወደ 20 በመቶ ዝቅ ማድረግ ተችሏል ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ከአጠቃላይ ሀብቱ ከፍተኛ መዋዕለ ንዋይ የወጣባቸው የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች 28 በመቶ ድርሻ ያላቸው መሆኑንም ሥራ አስፈፃሚው አስታውቀዋል፡፡

25 ነጥብ 5 በመቶው አጠቃላይ ሀብት ደግሞ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች፣ የከፍተኛ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች እና የስዊች ያርድ ድርሻ መሆኑን የገለፁት አቶ ደመረ የ150 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ዋጋ ያላቸው ናቸው ብለዋል፡፡

ቀሪው 46 ነጥብ 5 በመቶ ሀብት ተሽከርካሪዎች፤ ህንፃዎች እንዲሁም ሌሎች ቋሚ እና ተንቀሳቃሽ ንብረቶችን ያጠቃለለ ነው፡፡

ተቋሙ በ2006 ዓ.ም እንደ አዲስ ሲቋቋም 34 ነጥብ 768 ቢሊዮን ብር የተከፈለ ካፒታል በመያዝ እንደነበር ያስታወሱት አቶ ደመረ ይህ አኀዝ በብዙ እጥፍ በማደጉ አዋጁን ማሻሻል እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከ19 በላይ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች፤ 20 ሺህ ኪ.ሜ ርዝመት ያላቸው የከፍተኛ ኃይል ማስተላለፈያ መስመሮች፤ ከ144 በላይ የኃይል ማከፋፈያ ጣቢያዎች በርካታ ህንፃዎች እና ከ900 በላይ ተሽከርካሪዎች አሉት፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ – ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም

Scroll to Top