በበጀት ዓመቱ አምስት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ታቅዷል

በበጀት ዓመቱ አምስት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ ታቅዷል

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2017 በጀት ዓመት የኃይል ማስተላለፊያ እና ማከፋፈያ ጣቢያዎችን ጨምሮ አምስት ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት የአላማጣ – ኮምቦልቻ – ለገጣፎ ባለ 230 ኪሎ ቮልት 2ኛ ሰርኪዩት ዝርጋታ፤የበቆጂ እና ደብረ ታቦር ማከፋፈያ ጣቢያ፤ የኮተቤ ግቢ ዕድሳት እና ማሻሻያ ፕሮጀክቶችን ለማጠናቀቅ እየተሰራ ነው፡፡

በተጨማሪም የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ዕድሳት እና የማሻሻያ ሥራ ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ መታቀዱን አስታውቀዋል፡፡

የደቡባዊ ግሪድ ማስፋፊያ እና የገዳ ስፔሻል ኢኮኖሚክ ዞን 230 ኪ.ቮ የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ፕሮጀክቶችን 75 በመቶ ለማድረስ እንደሚሰራም ነው የገለፁት፡፡

በሌላ በኩል የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ 99.4 በመቶ፤ የኮይሻ ሀይል ማመንጫ ፕሮጀክት 73.96 በመቶ፤ የአይሻ ንፋስ ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክትን 95.58 በመቶ ለማድረስ መታቀዱንም ነው አቶ አሸብር ያስታወቁት፡፡

ፕሮጀክቶቹ ተጠናቀው አገልግሎት መስጠት ሲጀምሩ የኃይል መቆራረጥን ከመቀነስ ባሻገር የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነትን እንደሚያሳድጉ ዋና ሥራ አስፈፃሚው ገልፀዋል፡፡

? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ይፋዊ የማኅበራዊ ትስስር ገጾችን በመቀላቀል ትኩስ መረጃዎችን በፍጥነት ያግኙ
ፌስቡክ↠ https://www.facebook.com/Ethioelectric
ቴሌግራም↠ https://t.me/EEPCommuication
ትዊተር ↠ https://twitter.com/EEPethiopia
ዩትዩብ ቻናል↠ https://www.youtube.com/@ethiopowermedia
ቲክቶክ አካውንት↠https://tiktok.com/@ethio_power
ድረ – ገፃችንንም ይጎብኙ www.eep.com.et
መስከረም 4 ቀን 2017 ዓ.ም

Scroll to Top