የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

የተቋሙ ከፍተኛ የሥራ አመራር አባላት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የአረንጓዴ አሻራቸውን አኖሩ

በተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ የተመራ ከፍተኛ የሥራ አመራር ቡድን “በጎነት ለኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተካሄደ ባለው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ላይ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል አሪ እና በደቡብ ኦሞ ዞኖች ተገኝቶ ችግኝ ተክሏል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደገለጹት ተቋሙ የሚያከናውናቸው የማኅበራዊ ኃላፊነት የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እና የአረንጓዴ አሻራ ሥራዎች ብሔራዊ አንድነትንና ወንድማማችነትን ለማጠናከር ትልቅ ድርሻ አላቸው።

በሁለቱ ዞኖች የተከናወኑት የቅድመ-አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች እና የመኖሪያ ቤቶች ግንባታ፣ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፎች ተቋሙን ከማስተዋወቅ ባሻገር ነገ የተቋሙ ተረካቢ በሚሆኑ ተማሪዎችና በህብረተሰቡ ዘንድ የባለቤትነት ስሜት የሚፈጥሩ መሆኑን ገልጸው በጎ አድራጎቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የዋና ሥራ አስፈጻሚ ጽሕፈት ቤት አቶ ሙላት ገዛኸኝ በበኩላቸው የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫዎች በዋናነት በውኃ ላይ የተመሰረቱ በመሆናቸው ግድቦች በደለል እንዳይሞሉና ዘላቂ የውኃ ምንጭ እንዲኖር የችግኝ ተከላ ሥራው ቁልፍ ተግባር መሆኑን አብራርተዋል።

ይህም ተቋሙ የሚገነባቸው የኃይል መሠረተ ልማቶች በደለል እንዳይሞሉና አስተማማኝ ኃይል እንዲያመንጩ አቅም እንደሚፈጥር ገልፀዋል።

የኮርፖሬት ገቨርናንስና ኮምፕሊያንስ ሥራ አስፈጻሚው አቶ ድጉማ ነዳ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ትልልቅ የኃይል መሠረተ ልማቶች የሚገኙበት በመሆኑ በዘንድሮው ክረምት ከአካባቢው ህብረተሰብ ጋር በመቀናጀት የአረንጓዴ የክረምት በጎ ፈቃድ  አካነውነናል።

ይህም ተቋሙ ከተሰጠው የኃይል ማመንጨትና ማቅረብ ተልዕኮ ጎን ለጎን በተለያዩ የልማት ስራዎች ላይ በመሳተፍ ተቋሙ ለሀገሪቱ ሁለንተናዊ እድገት እያበረከተ ያለውን ሂደት የሚያሳይ ነው ብለዋል።

Scroll to Top