ተቋሙ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎችን አስጀመረ

ተቋሙ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የልማትና የበጎ አድራጎት ሥራዎችን አስጀመረ

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣትና የልማት ፍትሃዊነትን ለማረጋገጥ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአሪ ዞን የበጎ ፈቃድ አገልግሎት መርሃ ግብር አካሂዷል።

በመርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ በአሪ ዞን ሦስት ደረጃቸውን የጠበቁ ትምህርት ቤቶችን እና አራት የአቅመ-ደካማ መኖሪያ ቤቶችን ለመገንባት የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

ዋና ሥራ አስፈጻሚው ባደረጉት ንግግር ተቋሙ ከኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ግንባታ ጎን ለጎን የኃይል ማመንጫዎችና ማከፋፈያ ጣቢያዎች በሚገኙበት አካባቢ የሚኖሩ ማህበረሰቦችን ቀጥተኛ ተጠቃሚ የሚያደርጉ የተለያዩ ማህበራዊ አገልግሎቶችን እያከናወነ ይገኛል።

ቀደም ሲል በአማራ ክልል ደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ ከ28 ሚሊዮን ብር በላይ በሚሆን ወጪ ለስድስት አቅመ-ደካማ ዜጎች ደረጃው የጠበቀ ባለአንድ ወለል ህንፃ ገንብቶ ለማስረከብ በዝግጅት ላይ እንደሚገኝና ለ250 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁስ ማከፋፈሉን እንደማሳያ ጠቅሰዋል።

በዛሬው ዕለትም በአሪ ዞን ጆንካ ከተማ በተካሄደው መሰረት ድንጋይ በተጨማሪ ለ60 ተማሪዎች የትምህርት ቁሳቁሶች ድጋፍና የችግኝ ተከላ መርሃ ግብርም ተካሂዷል።

እነዚህ የልማት ሥራዎች ብሔራዊ አንድነትን፣ ወንድማማችነትንና አካታችነትን ለማጠናከር ያለሙ መሆናቸውን የገለጹት ኢንጂነር አሸብር በአሪ ዞን የተጀመረው የበጎ አገልግሎት መርሃ ግብር በተመሳሳይ በነገው ዕለት በደቡብ ኦሞ ዞንም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ሥራ አስፈፃሚው ተናግረዋል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top