የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ከዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በመጀመሪያ ዲግሪ ያስተማራቸውን 47 የጊቤ አንድ እና ሁለት ኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች እንዲሁም የደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሠራተኞች የምረቃ ሥነ-ሥርዓት በጊቤ አንድ የውኃ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ ግቢ ውስጥ እየተከናወነ ይገኛል።


ከተመራቂዎቹ መካከል 29 የሚሆኑት ከጊቤ አንድ፣ ዘጠኝ ከጊቤ ሁለት ኃይል ማመንጫ ጣቢያ እንዲሁም 9 ደግሞ ከደቡብ ምዕራብ ሪጅን የተውጣጡ ሲሆኑ ከአጠቃላይ ተመራቂዎች ውስጥ 11 ሴቶች ናቸው።
ዩኒቨርሲቲው ሠራተኞችን ሲያስመርቅ ይህ ለሁለተኛ ጊዜ ሲሆን የዛሬ ተመራቂ ሠራተኞች በኤሌክትሪካል እና ኮምፒዩተር ኢንጅነሪንግ የትምህርት መስክ ከመደበኛ ሥራቸው ጎን ለጎን በሥራ ቦታቸው ላይ ሆነው ትምህርታቸውን በተከታታይ የትምህርት ፕሮግራም ለአምስት ዓመታት ሲከታተሉ የቆዩ ናቸው።
በምረቃ ሥነ-ሥርዓት ላይ በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የጀነሬሽን ቢዝነስ የኃይል ማመንጫዎች ማስተባበሪያ አንድ ዳይሬክተር አቶ አብዱ ይማም፣ የዋቻሞ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ተወካይ እና የዩኒቨርሲቲው የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር አዳነ ወ/መድህን (ዶ/ር)፣ የጣቢያዎቹና የሪጅኑ የሥራ ኃላፊዎች፣ የዩኒቨርሲቲው የሴኔት አባላት፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።
የኮርፖሬት ኮሙዩኒኬሽን መምሪያ በቦታው ተገኝቶ የምረቃ ሥነ-ሥርዓቱን እየተከታተለ የሚገኝ ሲሆን ተጨማሪ መረጃዎችን በቀጣይ የሚያደርስ ይሆናል።


