ዘርፉ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ግንባታ በማጠናቀቅ ላይ ነው

ዘርፉ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ግንባታ በማጠናቀቅ ላይ ነው

ተቋሙ የማህበራዊ አገልግሎት ተልዕኮውን ለመወጣት በደሴ ከተማ እያስገነባ የሚገኘውን የአቅመ ደካማ መኖሪያ ቤት ግንባታ በማጠናቀቅ ላይ መሆኑን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኢንጂነሪንግ እና ኮንስትራክሽን ዘርፍ አስታወቀ።

በዘርፉ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አቶ ቴዎድሮስ ከፈለኝ እንደገለፁት ተቋሙ ለስድስት አቅመ ደካማ አባዎራዎች መኖሪያ የሚውሉ እያንዳንዳቸው 42 ካሬ ሜትር ስፋት ያላቸው ስድስት ባለ አንድ መኝታ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እየገነባ ነው፡፡

እንደ ሥራ አስኪያጁ ገለፃ ተቋሙ በ28.2 ሚሊዮን ብር ወጪ እያስገነባ ያለው ባለ አንድ ፎቅ (ጂ+1) ህንፃ የመኖሪያ ቤት ግንባታ 98 በመቶ ደርሷል፡፡

ግንባታቸው ሙሉ በሙሉ ሲጠናቀቅ የተቋሙ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እና የደሴ ከተማ አስተዳደር አመራሮች በተገኙበት ለተጠቃሚዎች እንደሚተላለፉ አቶ ቴዎድሮስ አስረድተዋል፡፡

ተቋሙ በኃይል ዘርፍ እያከናወነ ከሚገኘው ዋና ተልዕኮ ባሻገር የማህበራዊ ኃላፊነት ማስፈፀሚያ ፖሊሲ በማዘጋጀት በመላ ሀገሪቱ የማህበራዊ አገልግሎት ኃላፊነቱን እየተወጣ ይገኛል።

💡 “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”

Scroll to Top