የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የ2018 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2019 በጀት ዓመት ዕቅዱን ከሥራ መሪዎች ጋር በስካይ ላይት ሆቴል መገምገም ጀምሯል።
በግምገማው ማስጀመሪያ ላይ የተቋሙ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ እንደገለጹት የግምገማ መድረኩ በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶችን እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶችን በመለየት ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ ያለመ ነው።
ያለ አስተማማኝ የኃይል አቅርቦት የሀገር ዕድገትና ብልፅግና የሚታሰብ ባለመሆኑ ተቋሙ የተጣለበትን ሀገራዊ ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት የአመራሩ ሚና ከፍተኛ መሆኑንም አንስተዋል።


ኢትዮጵያ ካሏት ግዙፍ ተቋማት መካከል የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ግንባር ቀደሙ መሆኑን የጠቆሙት ዋና ሥራ አስፈጻሚው በዚህ ተቋም ማገልገልና ለተሻለ ውጤት መትጋት እንደ ክብር ሊታይ የሚገባው ነው ብለዋል።
በበጀት ዓመቱ የተመዘገቡ ስኬቶችና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንዲሁም ተቋሙ ያልተሻገራቸው ድክመቶች መኖራቸውንም አስታውሰዋል።
የተቋሙ አመራሮችም በስኬቶቹና በተግዳሮቶቹ ላይ የጋራ ግንዛቤ በመያዝ ለተሻለ ውጤት መስራት እንዳለባቸው አሳስበዋል።
በቀጣይ በበጀት ዓመቱ የተሻለ ውጤት ያስመዘገቡ የሥራ ክፍሎችና ሠራተኞች የዕውቅናና ሽልማት ሥነ-ሥርዓት ለማካሔድ ዕቅድ መያዙን ጠቁመዋል።
በግምገማ መድረኩ የሁሉም ዘርፎች የበጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የቀጣይ በጀት ዓመት ዕቅድ የሚቀርብ ይሆናል።




