የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል በ2018 በጀት ዓመት ከ35 ሺህ 670 ጊጋ ዋት ሰዓት በላይ ኃይል ማመንጨቱን የጀነሬሽን ቢዝነስ ዘርፍ አስታወቀ።
የዘርፉ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ ኢንጂነር ኤፍሬም ወ/ኪዳን እንደገለፁት በበጀት ዓመቱ 38 ሺህ 124 ነጥብ 78 ጊጋ ዋት ሰዓት ለማምረት ታቅዶ 35 ሺህ 670 ነጥብ 99 ጊጋ ዋት ሰዓት ኃይል ማምረት ተችሏል።

ይህም የዕቅዱን 93 ነጥብ 6 በመቶ መሆኑንና ከ2017 በጀት ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ከተመረተው ኃይል ጋር ሲነፃፀር የ21 በመቶ ዕድገት ያለው መሆኑን አብራርተዋል።
እንደ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ በበጀት ዓመቱ ከመነጨው ኃይል ውስጥ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ የኃይል ማመንጫ ጣቢያ 51 ነጥብ 5 በመቶ እንዲሁም የጊቤ ሦስት እና የበለስ የኃይል ማመንጫ ጣቢያዎች የ17 ነጥብ 8 እና የ7 በመቶ ከፍተኛ ድርሻ እንደነበራቸው አንስተዋል።

