የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አመራሮችና ሠራተኞች “የመሀል ዘመን” በሚል መሪ ሀሳብ በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ዉይይት ማድረግ ጀምረዋል።
የለውጥ ወጥመዶች እና የመሻገር ሂደቶች ላይ ባተኮረው የዉይይት መድረክ ላይ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ተስፋሁን ጎበዛይ በመንግስት የተዘጋጀውን የመወያያ ርዕሰ ጉዳይ አቅርበዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የኢትዮጵያ ኢንሸስትመንት ሆልዲንግ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ብሩክ ታዬ (ዶ/ር)፣ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ አክሊሉ ታደሰ፣ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኢንጂነር አሸብር ባልቻ፣ የኢትዮጵያ ኢንሸስትመንት ሆልዲንግ የኢነርጂ ዘርፍ ዳይሬክተር ጌትነት መላክ(ዶ/ር) ጨምሮ ከስምንት መቶ በላይ የዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች በመሳተፍ ላይ ናቸው።
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”


