የሴቶችን አሳታፊነት እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል

የሴቶችን አሳታፊነት እና ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ይገባል

ዓለም አቀፉ የሴቶች ቀን በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የተለያዩ ሪጅኖች መከበሩን የሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ገለጸ፡፡

የመምሪያው ዳይሬክተር ወ/ሮ ሌንሴ ኢደኤ እንደተናገሩት የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን ከዋና መ/ቤቱ በተጨማሪ በገናሌ ዳዋ ኃይል ማመንጫ ጣቢያ፣ በደቡብ ምዕራብ ሪጅን፣ በመካከለኛ 1 እና 2 ሪጅኖች እና በደቡብ 1 ሪጅን በተለያዩ ዝግጅቶች ተከብሯል፡፡

የተቋሙ ሴት ሠራተኞች ተፈጥሮአዊ እና ሌሎች ሰው ሰራሽ ልዩነቶች ሳያግዳቸው በአስቸጋሪ የሥራ ቦታዎች ጭምር ውጤታማ ሥራ እያከናወኑ መሆኑን አስታውሰዋል፡፡

ሴት ሠራተኞች ያሉባቸው ችግሮች በዘላቂነት ተቀርፈው በሁሉም መስክ ተጣቃሚነታቸውን እና ተሳታፊነታቸውን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት ውስጥ በግንባር ቀደምትነት ተሰልፈው የበኩላቸውን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡

በዓሉ በተለያዩ ትምህርታዊ ጉብኝቶችና ውይይቶች እንዲከበር ትብብር ላደረጉ የሥራ ኃላፊዎችም ዳይሬክተሯ ምስጋና አቅርበዋል።

Scroll to Top