ተቋማችን ዛሬ በመላው ሀገሪቱ የሲስተም ማሻሻያ ሥራ ሲያከናውን በአንዳንድ አካባቢዎች ለተወሰኑ ደቂቃዎች የኃይል መቋረጥ አጋጥሞ ነበር።
የማሻሻያ ሥራው ነገ እሁድ የማይከናወን መሆኑን ከወዲሁ እየገለፅን ሥራው በሚሰራባቸው ዕለታት አስቀድመን የምናሳውቃችሁ ይሆናል።
የማሻሻያ ሥራው እስኪጠናቀቅ ድረስ በትዕግስት እንድትጠብቁን ጥሪያችንን እናቀርባለን።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል
“ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”