በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የሕግ አገልግሎት መምሪያ በሁሉም የሥራ ዘርፎች ሕግና መመሪያን መሠረት ያደረገ የአሠራር ሥርዓት ለማስፈን ቁርጠኛ መሆኑን የመምሪያው ተወካይ ዳይሬክተር አስታወቁ።
ዳይሬክተሯ ወይዘሮ መስከረም በቀለ እንደገለፁት የሥራ ክፍሎች ላቀረቡት 166 የሕግ ድጋፍና ምክር ጥያቄ ተገቢ ድጋፍ ተደርጓል፡፡
መምሪያው የባለሙያዎችን አቅምን በማሳደግ የተቋሙን ጥቅም ለማስጠበቅ፣ ገጽታውን ለመገንባትና መልካም ስሙን ለማጎልበት እንደሚሰራ ዳይሬክተሯ አረጋግጠዋል፡፡
በተቋሙ ውስጥ ንቃተ ህግ እንዲያድግ በማድረግ የህግ ተገዢነትን ማሳደግ ትኩረት የሚሰጠው መሆኑንም ወ/ሮ መስከረም ተናግረዋል፡፡
? “ንፁህ ኢነርጂ ለተሻለ ህይወት!”